የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲንና የህንዱ ጠ/ሚ ሞዲ በኒው ዴህሊ ተገናኝተው ተወያይተዋል
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው እለት ተገናኝተው ተወያይተዋል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህንዷ ኒው ዴህሊ ከተማ እየተካሄደ ባለው 21ኛው የሩሲያ ህንድ ዓመታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው ተገናኝተው የተወያዩት።
መሪዎቹ በነበራቸው ቆይታም በሀገራቱ መካከል በንግድ እና በወታደራዊ ዘፍር ባለው ግንኝነት እንዲሁም በአፍጋኒስታን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸውን የህንድ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል።
በውይይታውም ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ሞስኮ ኒው ደልሂን በፈተና ጊዜ አብሮ የሚቆም እንደ ታላቅና ኃይል ወዳጅ አገር ትወስዳለች ብለዋል።
ከሁለቱ መሪዎች ውይይት ቀደም ብሎም ህንድና ሩሲያ የ600 ሺህ “የAK-203” ክላሽንኮቭ መሳሪያ ግዢ ስምምነት መፈራረማቸውም ተነግሯል።
ስምምነቱንም የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሺዮጉ እና የህንዱ የመከላከያ ሚኒስትር ራጃንታ ሲንግ መካካል መፈረሙም ታውቋል።
ሲጠበቅ የነበረው ስምምነቱ ሩሲያ እና ህንድ የጦር መሳሪያዎችኑ በህንዷኡታ ፓርዴሽ ግዛት ውስጥ በጋራ እንዲያመርቱ የሚያስችላቸው እንደሆነም ተነግሯ።
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭም ዛሬ ረፋ ላይ በሰጡት መግለጫ በሩሲያ እና በህንድ መካካል የተፈረመው የኤስ 400 የአየር መቃወሚያ የሚሳዔል ስርዓት ግዥ ስምምነት ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቀዋል።
አሜሪካ ስምምነቱን ለማፍረስ በርካታ ሙከራዎችን ብታካሂድም፤ ሙከራዋ አለመሳካቱን እና አሁን ላይ ስራ ላይ እየዋለ እንደሆነም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ያስታወቁት።