“አረብ ኢሚሬትስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተማማኝ የኃይል አቅራቢ ሆና ትቀጥላለች”- ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ
ፕሬዝዳንቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አቅማችንን ማዳበር ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ዘርፎች አንዱ ነው ብለዋል
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ የመጀሪያ ንግግራቸውን አድርገዋል
የተባሩት አረብ ኢሚሬትስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተማማኝ የኃይል አቅራቢ ሆና ለመቀጠል እንደምትሰራ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ ገለጹ።
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ የተባሩት አረብ ኢሚሬትስ አረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሸሙ በኋላ የመጀመሪያ ንግግራቸውን ዛሬ አድርገዋል።
በመጀመሪያ ንግግራቸውም የፌዴሬሽኑ ጠቅላይ ምክር ቤት አባላት ለሰጣቸው ትልቅ ኃላፊነት ያመሰገኑት ፕሬዝዳንቱ፤ በኢኮኖሚ፣ በኃይል ዘርፍ፣ በፖለቲካ፣ በደህንነት እና በማህረባሪ ጉዳዮች ላይ የመንግስታቸውን አቅጣጫ ግልጽ አድርገዋል።
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ በንግግራቸው “መንግስታችን ትኩረት እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የዜጎች ምቾት፣ ደስታ እና እንክብካቤ አመስጠት ነው፤ ይህ በወደፊት እቅዶቻችን ሁሉ መሰረት ሆኖ ይቆያል” ብለዋል።
የተባበሩት ኢሚሬቶች ነዋሪዎች በመሬታችን ላይ ለግንባታ እና ልማት የሚያደርጉትን ቀጣይነት ያለው ጥረት ዋጋ እንሰጣለን” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “በኢሚሬትስ ሰዎች ያለን መተማመን እና ኩራት ገደብ የለውም” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አክለውም፤ “የአረብ ኢምሬትስ ሉዓላዊነትና ደህንነት ለድርድር የማይቀርብ መሰረታዊ ጉዳይ ነው” ሲሉም ተናረዋል።
በኃይል አቅርቦት ዘርፍም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አስተማማኝ የኃይል አቅራቢ ሆና እንደምትቀጥል ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ የአለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነት አጋር በመሆን የአገሪቱን አቋም አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል።
“በዓለም ዙሪያ በበጎ አድራጎት ስራ ሀይማኖት፣ ዘር እና ቀለም ሳንገደብ ግንባር ቀደምትነት ያለንን ሚና ለማጠናከር እንሰራለን” ሲሉም ገልፀዋል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዘይድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ወንድማቸውን ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያንን ተክተው ነው ባሳለፍነው ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ/ም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡት።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መስራች ፕሬዝዳንት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን ሶስተኛ ልጅ ሲሆኑ የተወለዱትም በመጋቢት 11 ቀን 1961 አል ዐይን በተባለው የአቡ ዳቢ አካባቢ ነው።
ሼክ መሀመድ በሀገሪቱ ፈጣንንና ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ትልቅ አሻራ ካኖሩና በቅድሚያ ከሚጠቀሱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሪዎች በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።
በተለይም ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ሳንደኸርስት ሮያል ወታደራዊ አካዳሚ ከተመረቁበት ከፈረንጆቹ ከ1979 ጀምሮ የዩኤኢን ጦር ሃይል በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉና እንደፈረንጆቹ ጥር 2005 የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሆኖው እስከመሾም የደረሱ ታላቅ መሪ ናቸው።
ሼክ መሀመድ በህዳር 2004 የአቡ ዳቢ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ለአቡ ዳቢ እድገት ጉልህ አስተዋፅዖን አበርክተዋል።