በጉባዔው የግብጽ፣ የኩዌት እና የኢራቅን ጨምሮ የሌሎችም ሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ
የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማት እና ደህንነት ጉባዔ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚካሄደ ይጠበቃል።
በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሳዑዲ አረቢያዋ ጂዳህ በመግበት ላይ እንደሚገኙም የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ሳዑዲ አረቢያ ጄዳሕ የገቡ ሲሆን፤ የሳዑዲ ልኡል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከሳዑዲ አረቢያ ልኡል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር መወያየታቸውም ተነግሯል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ እና ልኡካቸወም ሳዑዲ አረቢያ የገባ ሲሆን፤ በሳዑዲ ልኡል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የኩዌት ልኡል አልጋ ወራሽ ሼክ ሚሻል አል አህመድ አል ጃቢር እና ልኡካቸውም በገልፍ አሜሪካ ጉባዔ ለመሳተፍ ሳዑዲ ገብቷል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ከዚሚ ቀደም ብለው በትናትናው እለት ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ሲሆን፤ ከሳዑዲ ልኡል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር በትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በገልፍ-አሜሪካ ጉባዔ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።