ጆ ባይደን፤ አንጌላ ሜርክልን ማመስገናቸው ተሰማ
የጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጆ ባይደንን ጨምሮ ከ4 የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ጋር ሰርተዋል
አንጌላ ሜርክል እና ጆ ባይደን በሩሲያ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራትም መክረዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በስልጣን ዘመናቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብንት ወደ ዋሸንግተን ያቀኑትን የጀርመኗን መራሄተ መንግስት ማድነቃቸው ተሰምቷል።
ጆ ባይደንን ጨምሮ ከአራት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ጋር በኃላፊነት ሲሰሩ የነበሩትን ሜርክል ጠንካራ መሪ እንደሆኑ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ምስክርነት ሰጥተዋቸዋል።
በአሜሪካ ቤተ መንግስት መሪዎቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባይደን፤ ሜርክልን መርህ ያላቸው ጠንካራ መሪ መሆናቸውንና ለሰዎችን ክብር ከመቆም የማይቦዝኑ ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።
ባይደን፤ አሜርክል አድናቆታቸውን ከገለጹ በኋላ፤ ከሩሲያ እስከ ጀርመን የተዘረጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ጉዳይ እንዳሳሰባቸውም ገልጸዋል።
ኖርድ ስትሪም ቁጥር 2 የተሰኘው ይህ ነዳጅ ማስተላለፊያ ጉዳይ ሩሲያ በአውሮፓ ሀገሮች ላይ ተጽዕኖዋ እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል በሚል ባይደን ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም የተነሳ የነዳጅ ኃይል ሩሲያ፤ ዩክሬንን እና ሌሎች የአሜሪካ ወዳጅ ሀገራትን ማስገደድ እንዳትችል ተረግባራዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጠይቀዋል።
አንጌላ ሜርክልና ጆ ባይደን በዚህ የነዳጅ ማስተላለፊያ ላይ የተለየ አዲስ ነገር ባይናገሩም፤ የጀርመኗ መራሄተ መንግስት ግን ዩክሬን የነዳጅ መስመሩ መተላለፊያ መሆኗን በአወንታ መልኩ ተመልክተውታል።
ይሁንና ልክ እንደሌሎች ሀገራት ዩክሬንም ግዛታዊ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናገረ መናገራቸውን ዩኤስኤ ቱዴይ ዘግቧል።