ጆ ባይደን፤ ለታይዋን የ1 ነጥብ1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ በአሜሪካ ኮንግረስ ለማጸደቅ ማቀዳቸው ተገለጸ
ሽያጩ 60 ጸረ-መርከብ እና 100 የአየር ላይ ሚሳዔሎችን እንደሚያካትትም ተገልጿል
የአሜሪካ እቅድ በምስራቅ ታይዋን የተፈጠረውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል በመገለጽ ላይ ነው
ሽያጩ 60 ጸረ-መርከብ እና 100 የአየር ላይ ሚሳዔሎችን እንደሚያካትትም ተገልጿል
ጆ ባይደን፤ 60 ጸረ-መርከብ እና 100 የአየር ላይ ሚሳዔሎችን ያካተተ የ1 ነጥብ1 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለታይዋን ለመሸጥ የአሜሪካ ኮንግረስ ለማጸደቅ ማቀዳቸው ተገለጸ፡፡
በዚህም ለታይዋን ትልቅ ድጋፍ ያለው የጆ ባይደን አስተዳደር እና የህግ አውጭዎች ምክር ቤት፤ የባይደንን ጥያቄ በሚቀጥሉት ሳምንታት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ሮይተርስ ፖለቲኮ መረጃን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ያም ሆኖ የባይደን እቅድ፤ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በምስራቅ ታይዋን የተፈጸረውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል በመገለጽ ላይ ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ሃገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ታይዋን፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ አካባቢን ደህንነት ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው እርምጃዎች ስታመሰግንም ትደመጣለች፡፡
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ እና በአካባቢው ያለውን ደህንነትና ሰላም ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው "ተጨባጭ እርምጃዎች" በቅረቡ ማመስገኑ የሚታወስ ነው፡፡
ይህ ታዲያ ለቤጂንግ ሰዎች ጥሩ ዜና እንዳልሆነ በመነገር ላይ ነው፡፡
ቻይና፤ አሜሪካ ከዚህ በኋላ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷ ስትገልጽ እንደቆየች የሚታወስ ነው፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ዋሸንግተን በቻይና ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች እንደማይታገስ ገልጿል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን አሜሪካ፤ ቻይናን ለመያዝ ታይዋንን ከመጠቀም እንድትቆጠብም ማሳሰባቸውም አይዘነጋም፡፡
የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡