ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አጃይ ባንጋን ለዓለም ባንክ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት መረጡ
የሕንድ ዝርያ ያላቸው አጃይ ባንጋ የቀድሞ ማስተርካርድ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ነበሩ
ባንኩን ላለፉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዴቪድ ማልፓስ ከሀላፊነት ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሕንድ ዝርያ ያላቸው አጃይ ባንጋን ለዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት በእጩነት መረጡ።
የዓለም ባንክን ላለፉት አራት አመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዴቪድ ማልፓስ ከሰሞኑ በፈቃደኝነት ሁላፊነታቸውን እንደሚለቁ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
- ትራምፕ፥ የባይደን አስተዳደር በዩክሬን ምድር 3ኛውን የአለም ጦርነት ሊያስጀምር ነው ሲሉ ወቀሱ
- በያዝነው 2023 ዓመት የዓለማችን ኢኮኖሚ ብርቱ ፈተና እንደሚገጥመው ተገለጸ
ማልፓስ ለሀላፊነት መልቀቅ ያበቃቸው በተደጋጋሚ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሰጧቸው አስተያየቶች ትችቶን በማስከተላቸው ነው።
ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በፊት የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንሳዊ አይደለም የምወስደውም እርምጃ የለም ማለታቸውን ተከትሎ ከብዙ ወገኖች ትችቶችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል።
በዓለም ባንክ ትልቅ የአክስዮን ድርሻ ያላት አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባንኩን እንዲመሩ አጃይ ባንጃን በእጩነት አቅርበዋል ተብሏል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ በዘር ሀረጋቸው ሕንዳዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆኑት አጃይ ቡቢዝነስ ተቋማት ብዙ ልምድ አላቸው።
በዓለም ባንክ ውስጥ ከአሜሪካ በመቀጠል ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻ ያላት ጀርመን ባንኩ በሴት እንዲመራ ፍላጎት አላት ተብሏል።
ይሁንና በአሜሪካ እጩ ሆነው የቀረቡት የ63 ዓመቱ የቀድሞው የማስተርካርድ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ከሕንድ እና ሌሎች ሀገራት ድጋፍ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
የባንኩ ቦርድ አባላት ከአንድ ወር በኋላ በሚያደርጉት ጉባኤ ሹመቱን እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል ተብሏል።
በ189 ሀገራት የተመሰረተው የዓለም ባንክ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ቻይና፣ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ ፣ህንድ፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ጣልያን ደግሞ ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻ ያላቸው ሀገራት ናቸው።