ባይደን አረብ አሜሪካዊያን በጋዛው ጦርነት የሚሰማቸውን 'ህመም' እንደሚረዱ ገለጹ
የባይደን አስተዳደር ሚያዝያ የአረብ አሜሪካን ቅርስ ወር እንዲሆን አድርጎ የወሰነው በ2021 ነበር
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አረብ አሜሪካውያን ለእሰራኤል በሚደረገው ድጋፍ ምክንያት የሚሰማቸውን 'ህመም' እንደሚረዱ ገልጸዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አረብ አሜሪካውያን፣ አሜሪካ በጋዛው ጦርነት ለእሰራኤል በምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ምክንያት የሚሰማቸውን 'ህመም' እንደሚረዱ ገልጸዋል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ብዙ ሙስሊሞች እና አረቦች የዲሞክራቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተኩስ እንዲቆም እንዲያደርጉ እና የጦር መሳሪያ ለእሰራኤል መሸጣቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
"ትንሽ ቆም ብለን የአረብ አሜሪካውያን ቤተሰቦች በጋዛ ጦርነት የሚሰማቸውን ህመም መናገር አለብን" ሲሉ ባይደን በኃይትሀውስ በወጣው በአረብ አሜሪካውያን ወር ማስጀመሪያ ፕሮክላሜሽን ላይ ተናግረዋል።
ነገርግን ከባይደን የአርብ እለት መግለጫ ከሰአታት በኋላ አሜሪካ ለእስራኤል የቦምብ እና የጦር ጀት ሽያጭ ማጽደቁን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
ከአሜሪካ ድጋፍ በማግኘት እስራኤል ቀደሚ ሀገር ስትሆን አሜሪካም ከቀናት በፊት በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ተአቅቦ ከማድረጓ በፊት የቀረቡ በርካታ የጋዛ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳቦችን እንዳይጸድቁ ማድረጓ ይታወሳል።
የባይደን አስተዳደር ሚያዝያ የአረብ አሜሪካን ቅርስ ወር እንዲሆን አድርጎ የወሰነው በ2021 ነበር።
በአሜሪካ በኒው ዮርክ እና ሎስአንጀለስ ባሉ በአየርመንገዶች እና በድልድዮች አቅራቢያዎች ጨምሮ በበርካታ ቦታዎች በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቁ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእሰራኤልን ድንበር ጥስ ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት እስካሁን ከ32ሺ በላይ ፍልሴጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል ተብሏል።
አሜሪካ፣ ግብጽ እና ኳታር ተኩስ እንዲቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማድረግ እያደራደሩ ቢሆንም እስካሁን የተገኘ አዎንታዊ ለውጥ የለም።