የተመድ ባለሙያ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለው ዘመቻ ከዘርማጥፋት ጋር ይስተካከላል ብለው እንደሚያምኑ ለአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ምክርቤት ተናግረዋል።
የተመድ ባለሙያ እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች አሉ።
የተባበሩት መንግስታት(ተመድ) ባለሙያ እስራኤል ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በጋዛ እየፈጸመችው ያለው ዘመቻ ከዘርማጥፋት ጋር ይስተካከላል ብለው እንደሚያምኑ ለአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ምክርቤት ተናግረዋል።
ባለሙያዋ ሀገራት በእስራኤል ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥሉባት ጥሪ አቅርቀዋል።
በምክርቤቱ ስብሰባ ላይ ያልተገኘችው እስራኤል የባለሙያዋን ግኝት ውድቅ አድርጋለች።
"በሰው ልጅ ላይ ምን ያህል አስከፊ ነገር እየደረሰ መሆኑን ሪፖርት ማድረግ የእኔ ኃላፊት ነው" ሲሉ በወረራ በተያዙት ቦታዎች ላይ የተመድ የሰብአዊ መብት ባለሙያ የሆኑት ፍራንሴስካ አልባኔዝ በጄኔቫ በተካሄደው የተመድ የሰብአዊ መብት ምክርቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
በጋዛ ከ30ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጠቀሱት ባለሙያዋ በፍልስጤማውያን ላይ የዘርማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ለማመን የሚያስችሉ ግኝቷቶች አሉ ብለዋል።
ባለሙያዋ አባል ሀገሪት በእስራኤል ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣል ኃላፊነቸውን እንዲወጡ መማጸናቸው ገልጿል።
አይሁዶች በናዚ መጨፍጨፋቸውን ተከትሎ በ1948 የወጣው 'የጄኖሳይድ ኮንቬንሽን' ዘርማጥፋትን ጎሳን፣ ኃይለማኖት ወይም ሀገርን በከፊል ወይም ሙሉበሙሉ ለማጥፋት የሚፈጸም ተግባር ነው ብሎ ተርጉሞታል።
በጄኔቫ የሚገኘው የእስራኤል የዲፕሎማቲክ ልኡኩ ዘርማጥፋት የሚለውን ቃል መጠቀም እንዳበሳጨው እና ጦሬነቱ ከሀማስ ጋር እንጅ ከፍልስጤማውያን ጋር አይደለም ብሏል።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተቀሰቀሰው ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር ጥሶ በፈጸመው ጥቃት 240 ሰዎችን ማገቱን እና 1200 የሚሆኑትን ደግሞ መግደሉን ተከትሎ ነበር።
ባለሙያዋ እውነትን መፈለግ ሲገባቸው ላሳሳቱት እና ላዛቡት እውነታ የሚስማማ ደካማ የሆነ ሀሳብ አቅርዋል ሲል ልኡኩ ቅሬታውን ገልጿል።
እስራኤል በደቡብ አፍሪካም የዘርማጥፋት ክስ በአለምአቀፉ ፍርድ ቤት ቀርቦባት በመከራከር ላይ ትገኛለች።
የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በትናንትናው እለት በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ አጽቆታል።
የውሳኔ ሀሳቡ የጸደቀው የእስራእል አጋር የሆነችው አሜሪካ ድምጸ ተአቅቦ በማድረጓ ነው።አሜሪካ ባንጸባረቀችው አቋም የተቆጣችው እስራኤል፣ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞም ሰርዛለች።