አሜሪካ የ20 አመታት የአፍጋኒስታን ቆይታዋ በኋላ ጦሯን ማስወጣቷ እንደሽንፈት ስለተቆጠረ ትችት አስከትሎባታል
አሜሪካ የ20 አመታት የአፍጋኒስታን ቆይታዋ በኋላ ጦሯን ማስወጣቷ እንደሽንፈት ስለተቆጠረ ትችት አስከትሎባታል
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በትዊተር ገጻቸው“ጊዜው ሌሎች ሀገራትን መልሶ የመስራት ወታደራዊ ዘመቻ የሚቆምበት” ነው በማለት ሀገሪቱ በአፍጋኒስታን ላይ የወሰደችውን እርምጃ ትክክለኛነት ተከላክለዋል፡፡
አሜሪካ የ20 አመታት የአፍጋኒስታን ቆይታዋ በኋላ ጦሯን ማስወጣቷ እንደሽንፈት ስለተቆጠረ ትችት አስከትሎባታል፡፡ የአሜረካን ወታደሮች መወጣት ተከትሎ በአጭር ቀናት ውስጥ በአፍጋኒስታን የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረውና በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረው ታለባን ከ20 በኋላ ስልጣን መቆጣጠር ችሏል፡፡
“ትንሽ የሚባል ጦርነት፣ትንሽ የአደጋ ተጋላጭነት ወይም ትንሽ ወጭ ያለው ጦርነት የለም” ብለዋል ፕሬዘዳንት ባይደን፡፡ ፕሬዘዳንቱ እንዳሉት 20 አመታት ያስቆጠረውን የሶቆታ፤የመስዋእትና ስቃይ ምእራፍ በመዝጋት፤ ያለፈውን ሳይሆን የወደፊቱን የምናይበት ጊዜ ነው“ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ባይደን “ይህ ወሳኔ ትክክለኛ፣ የተጠናና ለአሜሪካ ምርጥ የሆነ ውሳኔ” ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
አሜሪካንን ጨምሮ አውሮፓውያን ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ በኋላ ዜጎቻቸውን እና ረዳቶቻቸውን ከሀገሪቱ እስከ ትናንት ድረስ ለማስወጣት በተስማሙት መሰረት አስወጥተዋል፡፡ አሜሪካና አውሮፓ ከዜጎቻቸው በተጨማሪ አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩትን የአፍጋኒስታን ዜጎች ከማስወጣት አልፈው ሌሎች ሀገራት እንዲቀበሏቸው አድርገዋል፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ካቡልን በተቆጣጠረበት ወቅት፣ ፍርሃት ያደረባቸው የአፍጋኒስታን ዜጎች በአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን ለመውጣት ሲሯሯጡ ታይተዋል፤ ብዙዎች ከሚበር አውሮፕላን ላይ ሲደውቁ ታይተዋል፡፡
በአፍጋኒስታን ይንቀሳቀሳል የሚባለው አይኤስ ቀደ ገደቡ ከማለፉ በፊት በካቡል አየርማረፊያ በነበሩት የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝሮ 11 ወታደሮችም መገደላቸው ይታወሳል፡፡