አይኤስ በካቡል ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን ጥቃት ይታደናሉ ብለዋል
ትናንት በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውጭ ላይ የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ አሜሪካ አሁንም ሌላ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሚችል በመጠርጠር በተጠንቀቅ ላይ መሆኗን አስታወቀች፡፡
ትናንትና አይኤስአይኤስ ኃላፊነቱን በተወሰደበት በዚህ ጥቃት 72 አፍጋናውያን እና 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ሌሎች ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ የዋሸንግትን ኮማንደሮች በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፍንዳታ ላይ የተሳተፉ ሃይሎችን እንደሚታደኑ ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ ኃላፊ እንደገለጹት የሀገራቸው ኮማንደሮች አይኤስ ሌሎች ጥቃቶችን ሊያደርስ ይችላል በሚል ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረጉ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በተለይም የሮኬት፣ ወይም በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦንድ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል በመጠርጠር ዝግጅት መደረጉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የማዕካዊ ኮማንድ ኃላፊው ጥቃቶች እንዳይደርሱ ከታሊባን ጋርም የደህንነት ልውውጥ እንደሚደረግ ገልጸው አንዳንድ ጥቃቶችንም በታሊባኖች እንደሚከሽፍ ገልጸዋል፡፡
የፔንታጎን ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ትናንትና ፍንዳታው መከሰቱን በትዊተር ማረጋገጣቸው የሚታወስ ሲሆን ምን ያህል ጉዳት ደረሰ? ምን ያህል ሰው ተጎዳ? የሚለው ግን እስካሁን በዝርዝር እንዳልታወቀ ገልጸው ነበር፡፡
አይኤስ በካቡል ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን ጥቃት እንደማይረሱት እና ፍንዳታውን የፈጸሙት ሰዎች እንደሚታደኑ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የካቡሉን ጥቃት አስመልክቶ ትናንት ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን በአፍጋኒስታን ወቅታዊ ሁኔታ ላይም ከጸጥታ ባለስልጣቻቸው ጋር ስብሰባ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
ታሊባን አፍጋንን መዲና ካቡል ከተቆጣጠረ 12 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን እስካሁን ከአፍጋኒስታን 100 ሺ ሰዎች ሀገራቸውን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡