ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “ታይዋን ከቻይና የሚቃጣባትን ማናቸውም ጥቃት ለመከላከል አሜሪካ ወደ ታይዋን ልታቀና ትችላለች”አሉ
ጆ ባይደን አታስቡ "ቻይና፣ ሩስያ እና የተቀረው ዓለም ፤ በዓለም ታሪክ እኛ እጅግ ኃያል ሀገር መሆናችን ያውቃልና" ብለዋል
ቻይና “አሜሪካ ታይዋን ወደ ጦርነቱ እንድትገባ እያስገደደቻት ነው፤ ግን አታተርፍበትም” ሲትል ምክር አዘል አስታየት ሰንዝራለች
ታይዋን ከቻይና የሚቃጣባትን ማናቸውም ጥቃት ለመከላከል አሜሪካ ወደ ታይዋን ልታቀና ትችላለች ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ፡፡
ቻይና የራሴ ነው በምትለው “ደሴት” ምክንያት ታይዋንና ቻይና መሳሳብ ውስጥ ከገቡ ሰነባብቷል፡፡ለዚህም ነው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ጉዳዩ ወደ ከፋ ሁኔታ ካመራ አሜሪካ ከታይዋን ጎን እንደምትሆን ተናግረዋል፡፡
"አዎ፡ እሱን ለማድረግ ቁርጠኛ ነን"ም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡ ሀገራቸው አሜሪካ በከፍተኛ የቻይና ወታደራዊና እና ፖለቲካዊ ጫና ስር የምትገኘውን ታይዋን ታግዛለች …? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፡፡
ዋሽንግተን፡ ታይዋን እራሷን ለመከላከል በሕግ ጣልቃ ልትገባ የምትችልበት ምክንያት ማቅረብ ቢኖርባትም ፣ የቻይና ጥቃት በሚደርስበት ጊዜ ታይዋን ለመጠበቅ በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የሚለውን ‹ስትራቴጂካዊ አሻሚ› ፖሊሲን ስትከተል ቆይታለች።
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር “አሜሪካ በታይዋን በምትከተለው ፖሊሲ ምንም ለውጥ እንደሌለና ቻይና የኔ ነው በምትላቸው ደሴቶች ላይ የሚቃጣውን ማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ ናት ሲል ባለፈው ነሃሴ ወር” መግለጹ ይታወሳል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሰዎች ስለ ዋሽንግተን ወታደራዊ አቅም ሊያሳስባቸው አይገባም ምክንያቱም" ቻይና፣ ሩስያ እና የተቀረው ዓለም ፤ በዓለም ታሪክ እኛ እጅግ ኃያል ሀገር መሆናችን ያውቃልና" ብሏል፡፡
"ሊያሳስባችሁ የሚገባው ነገር ቢኖር፤ እነሱ ከባድ ስህተት ሊሠሩ በሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ በሚያደርጉዋቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋሉ ወይስ አይስተፉም ? የሚለውን ነው" ሲሉም አክሏል ጆ-ባይደን፡፡
ጆ-ባይደን "ከቻይና ጋር ቀዝቃዛ ጦርነት አልፈልግም። ወደ ኋላ የምናፈገፍግበት ምክንያት የለንም ፣ ማንኛውንም አመለካከታችንን እንደማንቀይር ቻይና እንድትገነዘብ እፈልጋለሁ" ሲሉም ተናግሯል፡፡
ከ40 ዓመታት በላይ የዘለቀው የታይዋን እና የቻይና ወታደራዊ ውጥረት አሁን ላይ የከፋ ደረጃ እንደደረሰ እንዲሁም ቻይና እንደፈረንጆቹ 2025 “ሙሉ የተደራጀ ወረራ”ልትፈጽም እንደመትችል የታይዋኑ የመከላከያ ሚኒሰትር ችዩ ኩ-ቸንግ ያላቸውን ስጋት በዚህ ወር ገልጸው ነበር ፡፡
“ታይዋን ነጻ ሀገር ናት ስለዚህም ነጻነትዋንና ዴሞክራሲዋን የምታስከብር ይሆናል”ም ብሏል ሚኒስትሩ፡፡
ቻይና በበኩሏ ከአሜሪካ ጋር ባላት ግንኙነት የታይዋን ጉዳይ በጣም አስፈላጊው አጀንዳ ነው እናም በዋሽንግተን እና በታይፔ መካከል ያለው ግንኙነት “ትብብር” ነው የሚሉት ተሳስተዋል ስትል አውግዛለች፡፡
በተመድ የቻይና ተወካይ አምባሰደር ዣንግ ጁን ከታይዋን ጋር “ሰላማዊ ውህደትን” ለማምጣት እየተሰራ እንደሆነ እና በገዥው ዴሞክራሲያዊ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ አማካኝነትም ለ“ተገንጣይ ሙከራዎች” ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግሯል።
አምባሳደር ጁን "እኛ ችግር ፈጣሪዎች አይደለንም፤ በተቃራኒ እንደ አሜሪካ-የመሳሰሉ የተወሰኑ ሀገራት በታይዋን ያለውን ሁኔታ ወደ አደገኛ አቅጣጫ እንዲያመራ አደገኛ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው" ሲሉም ነው ያስጠነቀቁት፡፡
ጁን አክለው " በዚህ ወቅት እኛ ልንጠይቅ የሚገባን የሚመስለለኝ፤ አሜሪካ እንዲህ ዓይነቱን ተግባር እንድታቆም ነው፡፡ ታይዋን ወደ ጦርነቱ እንድትገባ የማንም አካል ፍለጎት አይደለም፡፡ አሜሪካም ብትሆን የምታተርፍበት ሁኔታ አልታየኝም"በማለት ምክር አዘል አስታየት ሰንዝሯል፡፡