ልዩልዩ
በታይዋን በደረሰው የባቡር አደጋ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 50 ደርሷል ተባለ
የአደጋው መንስዔ አንድ በአግባቡ ያልቆመ ተሽከርካሪ ወደኋላ ተጉዞ ከባቡሩ ጋር መጋጨቱ ነው
አደጋው ከ400 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች ባቡር ሃዲዱን ስቶ በመጋጨቱ ያጋጠመ ነው
ዛሬ ጠዋት በምስራቃዊ ታይዋን ሲጓዝ የነበረበትን ሃዲድ ስቶ በተጋጨ ባቡር በደረሰ አደጋ እስካሁን የ 50 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
አደጋው ከ400 በላይ ሰዎችን አሳፍሮሲጓዝ የነበረ ባለ 8 ፉርጎ ባቡር ‘ዳቂንግሹይ’ ከተባለ ዋሻ ውስጥ ሲገባ ሃዲዱን በመሳቱ ያጋጠመ ነው፡፡
እንደ ሃገሪቱ ባቡር መንገዶች አስተዳደር ባለስልጣን ገለጻ የባቡሩን ሹፌር ጨምሮ የ36 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል ፡፡
ሌሎች 61 ተሳፋሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር አሻቅቦ 50 መድረሱ ተረጋግጧል፡፡
እንደ ባለስልጣኑ ገለጻ ከሆነ የአደጋው መንስዔ አንድ በአግባቡ ቆሞ ያልነበረ ተሽከርካሪ ነው፡፡
ተሽከርካሪው በአካባቢው በሚገነባ አውራ መንገድ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን ፣ በአግባቡ እንዲቆም ባለመደረጉ ምክንያት ወደ ኋላ ተሽከርክሮ ከባቡሩ ጋር ሊጋጭና ባቡሩን ከሃዲዱ ሊያስወጣው ችሏል፡፡
የግንባታው ሰራተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በመመርመር ላይ ናቸው ታይዋን ኒውስ እንደዘገበው፡፡