የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ “አንድ ቻይና” የሚለውን መርህ የሚጥስ መሆኑን ቻይና ገልጻለች
የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ “አንድ ቻይና” የሚለውን መርህ የሚጥስ መሆኑን ቻይና ገልጻለች
አሜሪካ ለታይዋን መሳሪያ የመሸጥ እቅዷን ባስቸኳይ እንድታቆም መጠየቋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸ ሲሆን ቻይና ህጋዊና አስፈላጊ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል፡፡
በቻይና ይህን ያለችው ከአሜሪካ ጋር የፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ በገባችበት ወቅት ነው፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛዎ ሊጂያን ይህን መልስ የሰጡት አሜሪካ ለታይዋን ሶስት ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ልትሸጥ አስባለች የሚል ጥያቄ መነሳቱን ተከትሎ መሆኑን ሲጂሲኤን ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ አንድ ቻይና የሚለውን መርህ የሚጥስና፣የሶስት ቻይና አሜረካ የጋራ መግለጫ በእጅጉ የሚጥስ መሆኑንና የአለምአቀፍ መሰረታዊ መርሆችን የሚጥስ መሆኑን ዛዎ ተናግረዋል፡፡
ቻይና የአሜሪካ እንቅስቃሴ ከባድ መሆኑን እንድትገነዘብ ትፈልጋለች፤ አሜሪካ በአንጻሩ ለቻይና ማሳሰቢያ ቦታ አለመስጠቷ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡