ቤጅንግ በሉዓላዊነት እና በግዛታዊ አንድነቷ ላይ ያስቀመጠችው ቀይ መስመር ሊጣስ አይገባም ብላለች
ቤጅንግ ሉዓላዊነቷን ደፍራለች ባለቻት ሉቲኒያ የሚገኙትን አምባሳደሯን መጥራቷን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ሉቲኒያ በሀገሯ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በተጨማሪ ለታይዋን የውክልና ጽ/ቤት መፍቀዷ ሉዓላዊነትን መዳፈር መሆኑን ገልጿል፡፡የቻይና መንግስት፣ሉቲኒያ ያደረገችው ድርጊት እንዳሳዘናት ገልጻ በሀገሪቷ ያሏትን አምባሳደር መጥራቷን ገልጻለች፡፡
ሉቲኒያም በተመሳሳይ በቻይና የሚገኙትን አምባሳደሯን እንድትጠራ ፍላጎት እንዳላትም ነው ቤጅንግ የገለጸችው፡፡
በዓለም ላይ አንድ ቻይና ብቻ እንዳለ ያነሳው የቻይና ዋጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፤ የአንዲት ቻይና መርህ ሊከበር እንደሚገባ ገልጿል፡፡ የአንዲት ቻይና መርህ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ዕውቅና ያለው እና መግባባት ላይ የተደረሰበት ጉዳይ መሆኑም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል፡፡ መግለጫው፤ ቻይና ከሀገራት ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ የፖለቲካ መሰረት እንደሆነ እንደምታምንም ይገልጻል፡፡
የቻይና ሕዝብ እና መንግስት በሀገሪቱ አብሮነት እና አንድነት ላይ ጽኑ እምነት እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡ ቤጅንግ በሉዓላዊነት እና በግዛታዊ አንድነቷ ላይ ያስቀመጠችው ቀይ መስመር ሊታለፍ እንደማይገባም ነው ያስታወቀችው፡፡ የሉቲኒያ መንግስት የሰራውን ስህተት ሊያርመው እንደሚገባ የገለጸው የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈላጊውን ውሳኔ ማሳረፍ አለበትም ብላለች፡፡ ቻይና፤ የታይዋን ነጻነት በሚል የሚያቀነቅኑ የታይዋን ባለስልጣናት ጉዳዩ የሞተ እና ያለቀለት መሆኑን አስጠንቅቃለች፡፡ ይህ ጉዳይ የተገንጣይ አክቲቪስቶች እንደሆነም ቤጅንግ ገልጻለች አስጠንቅቃለች፡፡