አሜሪካ፤ የጃፓንን መከላከያ እንዲጠናከር እንደምትደግፍም ተገልጿል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ጃፓን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንድትሆን ድጋፍ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡
በእስያ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ባይደን፤ ቻይና በቀጠናው ያላትን ሃያልነት ከጃፓን ጋር ሆኖ መግታት እንደሚገባ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ቶኪዮ የመከላከያ ኃይሏን እንድታጠናክር ከአሜሪካ ጋር በቅርበት እንደምትሰራም ነው የተገለጸው፡፡
ጆ ባይደን ከምርጫ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ የሩቅ ምስራቅ ጉብኝት የጃፓንን የመከላከያ ኃይል ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ጽ/ቤታቸው (ኋይት ሃውስ) አስታውቋል፡፡
የጃፓን እና የአሜሪካ መሪዎች ባደረጉት ውይይት ቻይና የአካባቢ ስጋት እንደሆነች መግለጻቸው ነው የተገነገረው፡፡
ሩሲያ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች
ኤን. ኤች. ኬ የተባለው የጃፓን ሚዲያ እንደዘገበው ከሆነ ጆ ባይደን ጃፓን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንድትሆን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት፤ ከአባል ሀገሮቹ መካከል የተወሰኑት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል መሆን እንዳለባቸው ባለፈው ስብሰባው ቢገልጸም እስካሁን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሰማ ነገር የለም፡፡ ከዛ ቀድሞ ግን ጆ ባይደን ጃፓን ቋሚ አባል እንድትሆን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡
የባይደን ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ ‘ኳድ’ በሚል የተሰየሙትን የጃፓን፣ የአውስትራሊያ እና የሕንድ መሪዎችን ለማግኘት እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡
‘ኳድ’ የተባለው ስብስብ የኢንዶ ፓስፊክ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀፍ አካል ሲሆን አሜሪካ ከእስያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዛት ታምኖበት የተመሰረተ የሃገራት ግንኙነት ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ለመነጋር በተገናኙበት ወቅት፤ ሀገራቸው የጃፓንን መከላከያ ሰራዊት እንዲጠናከር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል አስታወቀች
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሺዳ የባይደን ንግግር፤ አሜሪካ በኢንዶ ፓስፊክ ቀጣና ያላትን ተሳትፎ ለማጠናከር እንደምትፈልግ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና አዲሱ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒስ ጃፓን በመገኘት ከባይደን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጆ ባይደን ትናንትና ከኮሪያ ተነስተው ጃፓን መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን ነገ ደግሞ ወደሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡