ፖለቲካ
የዱባይ ፖሊስ “አራት እስራኤላውያን በስለት ተወጉ” መባሉን አስተባበለ
የዱባይ ፖሊስ የሁሉንም ሰው ደህንንት ማስጠበቅ በአረብ ኢሚሬትስ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ብለዋል
የዱባይ ፖሊስ ሁሉም ሰው ምንጫቸው ካልተረጋገጠ ከሚወጡ ከአሉባልታና የውሸት ዜናዎች እንዲርቅ አሳስቧል
የዱባይ ፖሊስ “አራት እስራኤላውያን በዱባይ ውስጥ በስለት እንደተወጉ ተገርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል አስተባበለ።
በአረብ ኢምሬትሷ ዱባይ “አራት እስራኤላውያን በስለት ተወጉ” የሚል መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ የዱባይ ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል።
የከተማዋ ፖሊስ በይፋዊ የኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፤ እስራኤላውያን በስለት ተወጉ የሚለው መረጃ ሀሰት ነው ስል አስተባብሏል።
አረብ ኢምሬትስ የሁሉንም ሰው ደህንንት ማስጠበቅ ቅድሚያ የምትሰጠው ተግባር መሆኑንም የዱባይ ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል።
የዱባይ ፖሊስ ሁሉም ሰው ምንጫቸው ካልተረጋገጠ ከሚወጡ ከአሉባልታና የውሸት ዜናዎች እንዲርቅ አሳስቧል።
የሃማስ እና እስራኤል ግጭት እንዲቆምና ሁለቱም ወገኖች ወደ ንግግር እንዲመለሱ የጠየቀችው ኤምሬትስ ፈጣን የሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ በመወሰን ቀዳሚ መሆኗ ይታወሳል።
አቡዳቢ ሁለቱም ወገኖች ንጹሃንን ኢላማ ከሚያደርጉ ጥቃቶች እንዲታቀቡ አሳስባለች።
ግጭቱ የፍልስጤም እና እስራኤልን የአመታት ውጥረት ለማርገብ የሚደረጉ ቀጠናዊ እና አለማቀፋዊ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ያስቆማል በሚልም ተቃውሞዋን ማሰማቷ ይታወሳል።