ጆ ባይደን “ጽንፈኛ” ያሏቸውን ዶናልድ ትራምፕንና ደጋፊዎቻቸውን አስጠነቀቁ
ፕሬዝዳንት ባይደን፤ “ዶናልድ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ዲሞክራሲ አደጋ ላይ ጥለዋል” ሲሉ ከሰዋል
ዶናልድ ትራምፕ “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” ብለው ነበር
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸውን በጽንፈኝት ወነጀሉ።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፊላዴልፊያ ባደረጉት ንግግር "ጽንፈኛ የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ ዴሞክራሲን አደጋ ላይ ጥለዋል" ያሉ ሲሆን፣ በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ ያሉ "ጨለምተኛ" ሀይሎችን ለመከላከል ሁሉም አሜሪካውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ጆ ባይደን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በከሰሱበት ንግግራቸው "ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም አሜሪካን ዳግም ግዙፍ እናደርጋለን" የሚለውን አጀንዳ የሚደግፉ ሰዎች የአሜሪካን ህገ መንግት በመጣስ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ለመገርሰስ የጣሩ እና ሀገሪቱን ወደኋላ ለመመለስ ያቀዱ ናቸው ብለዋል።
"ትራምፕ እና አሜሪካን ዳግም ግዙፍ እናደርጋለን አጀንዳ ደጋፊ ሪፐብሊካኖች በጽንፈኝነት ይወከላሉ ያሉት ባይደን፣ ይህ ደግሞ ሪፐብሊኩን አደጋ ላይ የሚጥል እና የማንታገሰው ነው ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ጠንከር ያለው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ንግግር የተሰማው በአመየሪካ የነካከለኛው ዘመን ምርጫ ለማካሄድ ሁት ወራት ሲቀራት የተደረገ ሲሆን፣ ባህድን ይህንን ምርጫ ለሀገሪቱ መንታ መንገድ ላይ እንድትቂም ያደረገ ነው ብለዋል።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ ፕሬዝዳንት ጂ ባይደንን በተደጋጋሚ ሲወርፉ ይሰማል።
ትራምፕ ከወር በፊት ባደረጉት ንግግርም “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” ብለው እንደነበረ ይታወሳል።