ቱጃሩ ቢል ጌትስ ከአንዲት የኩባንያቸው ሰራተኛ ጋር ነበቸው የተባለ ፆታዊ ግንኙነት እየተጣራ ነው
ቢልየነሩ ከሰራተኛዋ ጋር ፆታዊ ግንኙነት እንደነበራቸው በሰፊው በመነገር ላይ ይገኛል
ቢል ጌትስ ከመሊንዳ ጋር የ27 ዓመታት የዘለቀውን ትዳራቸውን በቅርቡ በፍቺ መቋጨታቸው ይታወሳል
ሚስተር ቢል ጌትስ በማይክሮሶፍት ኩባንያ ትሰራ ከነበረች አንዲት ሴት ጋር ከ20 ዓመታት በፊት ፆታዊ ግንኙነት እንደነበራቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡
እናም ግዙፉ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቢሊዬነሩ ከሰራተኛዋ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ነበራቸው ተብሎ እየተንሰራፋ ስለሚገኘው ወሬ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የሮይቶርስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ የማጣራት ሂደቱ የተጀመረው በሰራተኛዋ ጥቆማ መሰረት ነው፡፡
ኩባንያው ክስ ላቀረበችው ሰራተኛው ከአንድ የህግ ተቋም ጋር በመሆን ድጋፍ እያደረገላት እንደሆነም ነው የገለጸው፡፡
ክሱ እየቀረበ ያለው ቢል ጌትስ ከኩባንያው የቦርድ አባልነት በተገለሉባትና ከባለቤታቸው መሊንዳ ጋር ፍቺ በፈጸሙበት ማግስት መሆኑ በርካቶችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ ምርመራው ከተጠቀሱት ጉዳዮች ጋር ምንም የሚያያዝ ነገር እንደሌለው ነው የኩባንያው ቃል አቀባይ የተናገሩት፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በ2019 ኩባንያው ሌላ አቤቱታ አስተናግዶ እንደነበርም በማስታወስ፡፡
የቢል እና መሊንዳ ለ27 ዓመታት የቆየ ትዳር በቅርቡ ባልተጠበቀ ፍቺ መቋጨቱ የሚታወስ ነው፡፡
የ65 ዓመቱ ጌትስ ፣ 4ኛው የዓለማችን ቢልየነር ሲሆኑ 124 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አላቸው፡፡