ቢል ጌት ሚስቱን መፍታቱ እንደሚቆጨው ተናገረ
የዓለማችን ባለጸጋ ቢል ጌት የትዳሬ መፍረስ የህይወት ዘመኔ ትልቁ ስህተቴ ነው ሲል ገልጻል
የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራቹ ቢል ጌት እና ሜሊንዳ ጌት ከ28 ዓመት ትዳር በኋላ ከሶስት ዓመት በፊት ተፋተዋል
ቢል ጌት ሚስቱን መፍታቱ እንደሚቆጨው ተናገረ።
ከዓለማችን ባለጸጋዎች መካከል አንዱ የሆነው እና የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራቹ ቢልጌት ስለ ህይወቱ ከታየምስ ኦፍ ለንደን ሚዲያ ጋር ቃለመጠይቅ አድርጓል።
ቢል ጌት በዚህ ጊዜ እንዳለው ከሶስት ዓመት በፊት በፍቺ የተጠናቀቀው ትዳሩ በመፍረሱ እንደሚጸጸት ተናግሯል።
ቢልጌት በትዳር ህይወቱ ሶስት ልጆች ማፍራቱን ገልጾ ይህ ትዳሩ መፍረሱ እንደሚቆጨውም ገልጿል።
በ1988 ዓ . ም የተጋቡት ሜሊዳ ጌት እና ቢልጌት ግንቦት 2013 ዓ.ም ትዳራቸውን በስምምነት አፍርሰዋል።
ለትዳሩ መፍረስ ደግሞ ቢል ጌት ከአንድ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ውስጥ ተቀጥራ ከምትሰራ ሴት ጋር መወስለቱን ተከትሎ ነው።
ቢል ጌት የትዳሩ መፍረስ የህይወት ዘመኑ ትልቁ ስህተት እንደነበርም በቃለ መጠይቁ ወቅት ተናግሯል።
ትዳሬ ቢፈርስም አሁንም ከቀድሞ ባለቤቴ ሜሊንዳ ጌት ጋር መልካም ግንኙነት አለኝ ሲልም ቢል ጌት አክሏል።
ስለልጆቻችን እና በጋራ ማድረግ ስላለብን የበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚነጋገሩ እና አብረው እንደሚሰሩም ተናግሯል።
ሁለቱ የቀድሞ ባልና ሚስቶች አሁን ላይ የየራሳቸው የፍቅር አጋር አላቸው የተባለ ሲሆን ቢልጌት ከቀድሞ ኦራክል ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፓውላ ኸርድ ጋር ፍቅር ውስጥ ነው ተብሏል።
እንዲሁም ሜሊንዳ ጌት ደግሞ ከታውቂው የንግድ ሰው ፊሊፕ ቫውጋን ጋር ፍቅር ውስጥ ናት ተብሏል።