አብዛኛው በጀት ለታዳጊ ሀገራት የጤና ስራዎች እንደሚውል ተገልጿል
ቢልጌት ለአንድ ዓመት ወጪ 9 ቢሊዮን ዶላር ገደማ በጀት መደበ፡፡
የ120 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ሀብት ያለው አሜሪካዊው ቢል ጌት በስሩ ለሚተዳደረው ጌትስ ፋውንዴሽን 8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ በጀት መመደቡን አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ እንዳለው ለያዝነው 2024 ዓመት ውስጥ ከመደበው 8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አብዛኛው በጀት ለታዳጊ ሀገራት የጤና ድጋፎች እንደሚውል ተገልጿል፡፡
የዘንድሮው ዓመታዊ በጀት በ2021 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ2 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡
ፋውንዴሽኑ በጀቱን ያሳደገው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የጤና ስራዎች በጀት ቅናሽ እያሳዩ በመምጣታቸው እንደሆነ ፋውንዴሽኑ አስታውቋል፡፡
የፋውንዴሽኑ ስራ አስፈጻሚ ማርክ ሱዝማን እንዳሉት ድርጅቱ በቀጣይ ዓመት ዓመታዊ በጀቱን በ2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጨምር ተናግረዋል፡፡
ቢልጌት እና የቀድሞ ባለቤቱ ሜሊንዳ በፈረንጆቹ 2000 ላይ ይህን ፋውንዴሽን የመሰረቱ ሲሆን የብዙዎችን ህይወት መቀየር የሚችሉ የጤና፣ አነስተኛ ግብርና እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዳቮስ 2024.. በዓለም ኢኮኖሚ የጠፋውን መተማመን መፈልግን አላማ ያደረገ ጉባዔ
በዓለም ችግሮች ዙሪያ የሚያተኩረው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ከዛሬ ጀምሮ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በመካሄድ ላይ ሲሆን ይህ ፋውንዴሽንም በመድረኩ ላይ እንደሚሳተፍ ገልጿል፡፡
የማይክሮሶፍት ኩባያ ባለቤት እና የዚህ ፋውንዴሽን መስራቹ ቡልጌት በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዳቮስ አምርቷል የተባለ ሲሆን አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ በጠየና ዘርፍ ስለሚያበረክተው ጥቅም ማብራሪያ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡