አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ የሚጠፋበትን ጊዜ ተነበዩ
ቢልጌት በፈረንጆቹ 2022 ቫይረሱ ሊጠፋ ይችላል ብለዋል
በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ደርሷል
አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ በ2022 ሊጠፋ ይችላ ሲሉ ተንብየዋል።
በፈረንጆቹ 2019 ታህሳስ ወር በቻይና ውሃን ግዛት የተነሳው ኮሮና ቫይረስ እስከ ዛሬ ድረስ ከ268 ሚሊየን በላይ ሰዎችን አጥቅቶ 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎችን ደግሞ ገድሏል።
ቫይረሱ በየጊዜው አዳዲስ ልውጥ ባህሪያትን ማሳየቱ የቫይረሱን ስርጭት እንዳይገታ ለማድረጉ የክትባት ተመራማሪዎች ይጠቅሳሉ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በደቡብ አፍሪካ የተገኘው ኦሚክሮን የተሰኘው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከ40 በላይ የዓለማችን አገራት ተከስቷል።
ይህ መሆኑ አሁንም ብዙዎች ቫይረሱ እንደ አዲስ ጉዳት ሊያደርስ ነው የሚል ስጋት የገባቸው ሲሆን ምዕራባዊያን አገራት በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢው አገራት ላይ የጉዞ እቀባ በመጣል ላይ ናቸው።
አሜሪካዊው ባለሀብት እና የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ መስራች ቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ ሊጠፋ የሚችልበትን ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
እንደ ቢል ጌትስ ትንበያ ከሆነ የኮሮና ቫይረስ በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ያበቃል።
“ኦሚክሮን የተሰኘው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት ስለ ቫይረሱ ማብቂያ ጊዜ መተንበይ ቢከብድም በ2022 ዓመት ቫይረሱ ያበቃል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።
የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ቫይረሱ ራሱን በመቀያየሩ ምክንያት ፋዋሽ ክትባት ለማምረት መፈተናቸውንም ቢልጌት ተናግረዋል።
ይሁንና አሁን ላይ በተለያዩ ተቀዋማት ተመርተው ለዜጎች በመሰጠት ላይ ያሉት ክትባቶች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ የቫይረሱን ጉዳት እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉንም ገልጸዋል።
የቢል ጌትስ ኩባንያዎች የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት ጊዜ ውስጥ 137 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማስገባታውንም ተናግረዋል።
ይሁንና በመጠናቀቅ ላይ ያለው የፈረንጆቹ 2021 ዓመት በህይወት ዘመኑ ፈታኝ እና ያልተለመደ ዓመት እንደሆነበት ቢልጌትስ ገልጿል።
አሁን ላይ በዓለም እየተሰራጨ ያለው የኮሮና ቫይረስ አዲስ ዝርያ አሳሳቢ ቢሆንም ዓለም ተጨማሪ አዲስ ልውጥ ዝርያ ቢከሰት ማስተናገድ በምትችልበት ደረጃ ላይ መሆኗን ቢለጌት በድረገጹ ባወጣው ጽሁፍ አክሏል።
የቢልጌት ከክትባት ጋር የተያያዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አፍሪካን እና ሌሎች ድሃ አገራት ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን እንዲያገኙ ከበለጸጉ ሀገራት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውንም ተናግሯል።