በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስህተት ምክንያት ለእስር የተዳረገው ሳይቲስት
የሳይንቲስቱ ፊት በግድያ ወንጀል ከሚፈለግ አንድ ተጠርጣሪ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተለይቶ ለእስር ተዳርጓል
የውሃ ምህንድስና ባለሙያው ከ20 ዓመት በፊት ተፈጽሟል በተባለው የግድያ ወንጀል ሊያዝ ችሏል
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስህተት ምክንያት ለእስር የተዳረገው ሳይቲስት
አሌክሳንድር ትስቬትኮቭ ሩሲያዊ ሲሆን የውሃ ምህንድስና ተመራማሪ መሆኑን ይናገራል፡፡ ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ ክራኖያርስክ ወደ ተሰኘችው የሩሲያዋ መዝናኛ ስፍራ እየተጓዘ እያለ በፖሊሶች ሊያዝ ችሏል፡፡
ይህ ተመራማሪ በፖሊሶች ለምን እንደተያዘ ሲጠይቅም ከ20 ዓመት በፊት በተፈጸመ የሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ መሆኑ ይነገረዋል፡፡
ወንጀሉን እንዳልፈጸሙ ለፖሊሶቹ ቢናገርም ሰሚ ያጣው ይህ ተመራማሪ ላለፉት 10 ወራት በእስር ቤት እንደቆየ ተገልጿል፡፡
ዘግይቶ በደረገው ማጣርትም የዚህ ሳይቲስት ፊት ግድያውን ትክክል ፈጽሞታል ከተባለው ተጠርጣሪ ጋር ያላቸው የፈት ቅርጽ ተመሳሳይ በመሆኑ ለእስር ሊዳረግ እንደቻለ ይረዳል፡፡
የዚህ ሳይንቲስት ፊትም ከትክክለኛው የግድያ ወንጀል ተጠርጣሪ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የተለየው በአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ መሆኑ ብዙዎችን እንዳስገረመ ተገልጿል፡፡
የተመራማሪው ቤተሰቦች እና የስራ ባልደረቦችም ወንጀሉ ተፈጽሞበታል በተባለው ስፍራ እንዳልነበር፣ ወንጀሉን እንዳልፈጸመ በርካታ ጥረቶችን ሲያደርጉ ቆይተው ከ10 ወር እስር በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ እንደተቀላቀለ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የመጀመሪያዋ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዲጄ ስራ ጀምራለች
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሰሞኑ ስለ ቴክኖሎጂው ባደረጉት ንግግር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውስብስብ ጉዳይ መሆኑን፣ በዚህ ጉዳይ ስህተት መፈጸም እንደሌለበት እና ለሚፈጸሙ ስህተቶችም ትክክለኛ መልስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡