
በዓለማችን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ከሆኑ ኩባንያዎች ጀርባ የባለጸጋዎች እጅ አለበት
የዓለማችን ባለጸጋዎች እና የገዟቸው ሚዲያዎች
በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ቀዳሚ የሚባሉት ባለጸጋ የሆኑ ግለሰቦች በሚዲያ እና ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው፡፡
ለአብነትም የአማዞኑ የሎጅስቲክስ ኩባንያ ባለቤቱ ጄፍ ቤዞስ ዋሽንግተን ፖስት የተሰኘው ሚዲያ ባለቤትም ናቸው፡፡
የ61 ዓመቱ እና 214 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ያለው ቤዞስ በአሜሪካ እና በመላው ዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነው ዋሸንግተን ፖስት ሚዲያን ገዝቷል፡፡
ሌላኛው የዓለማችን ባለጸጋ ሮበርት ሙርዶክ በአሜሪካ እና አውሮፓ በርካታ ሚዲያዎችን የተቆጣጠሩ ሲሆን ፎክስ ኒውስ፣ ኒዮርፕ ፖስት፣ ስካይ ኒውስ፣ዎልስትሪት ጆርናል እና ሌሎች ሚዲያዎችን በባለ ቤትነት እንደያዙ ናቸው፡፡
ሩሲያዊው ባለጸጋ አሌክሳንደር ለበዴቭ ዘ ኢንዲፐንደንት የተሰኘውን ጋዜጣ ሲቆጣጠር የቻይናዊው ጃክ ማ ከሎጅስቲክስ ኩባንያ ባለቤቱነቱ በተጨማሪ በእስያ ተነባቢው ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት የተሰኘውን ጋዜጣ በባለቤትነት ይዟል፡፡