የሕንድ እና የዓለማችን ባለጸጋ እስካሁን በአሜሪካ ስለቀረበበት ክስ ምላሽ አልሰጠም
አሜሪካ በሕንዱ ቁጥር ሁለት ባለጸጋ ላይ ክስ መሰረተች፡፡
የ58 ዓመቱ ህንዳዊ ጓታም አዳኒ በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋርጦ ከሚኖርባት ጉጃራት ወደ ሞምባይ ስራ ፍለጋ ከሄደ በኋላ ቀስ በቀስ አሁን ላይ የሕንድ ቁጥር ሁለት ባለጸጋ ሆኗል፡፡
አሁን ላይ የ70 ቢሊዮን ዶላር ሀብት እንዳለው የሚገለጸው ጓታም አዳኒ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው ተገልጿል፡፡
በኒዮርክ ያለው ፍትህ ቢሮ በትናንትናው ዕለት በአዳኒ ላይ የሙስና ቅሌት ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱ አዳኒ ከመንግስት ጋር በመመሳጠር ፍትሀዊ ባልሆኑ መንገዶች ጨረታዎችን ሲያሸንፍ ነበር ተብሏል፡፡
ሁለት ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላው ጨረታዎችን ያላግባብ አሸንፏል የተባለው ጓታም አዳኒ በወደብ ልማት፣ ታዳሽ ሀይል ልማት እና ኤርፖርቶች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እንዳሸነፈም ተገልጿል፡፡
ጓታም አዳኒ እስካሁን በአሜሪካ ስለተመሰረተበት ክስ ምላሽ አልሰጠም የተባለ ሲሆን የሕንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በተደጋጋሚ ትችታቸውን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል፡፡
በህንድ ገበያ የደራላቸው "የሌብነት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች"
አሜሪካ በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ከጀመረች ሁለት ዓመት ያስቆጠረች ሲሆን በወቅቱ ጓታም አዳኒ ፈጽሟል የተባለውን ወንጀል ውድቅ በማድረግ ምርመራውን ተቃውሞ ነበር፡፡
የህንድ ባለስልጣናት ለጓታም አዳኒ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ከአሜሪካ ኩባንያዎች ሳይቀር እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር በብድር እና በቦንድ ግዢ ገቢ እንዲያገኝ አድርገዋልም መባላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጓታም አዳኒ ከሰሞኑ ለዶናልድ ትራምፕ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸው በአሜሪካ ቢዝነስ ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉ እና ጠየ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለመክፈት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው ነበር፡፡