በሽታው በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ ተከስቷል ተብሏል
የወፍ በሽታ ወደ አዲስ ሀገራት መዛመት በዶሮ እርባታ ላይ ስጋት መፍጠሩ ተነገረ።
የአቪያን ፍሉ የተባለ የወፍ በሽታ የዓለም ማዕዘናትን አዳርሷል የተባለ ሲሆን፤ ቫይረሱ ወደ ዶሮ እርባታ በሚያስተላልፉ የዱር አእዋፍ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ተይቷል ተብሏል
የእንስሳት ሀኪሞችና የበሽታ ባለሙያዎች ዓመቱን ሙሉ እየተከሰተ ያለ ችግር ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሮይተርስ በአራት አህጉራት የሚገኙ ከ20 በላይ ባለሙያዎችን እና አርቢዎችን አነጋግሮ የቫይረሱ ስርጭት በዶሮ እርባታዎች ላይ ቶሎ እንደማይጠፋ ነግረውኛል ብሏል። ይህም በዓለም የምግብ አቅርቦት ላይ ስጋት እየፈጠረ ነው ብለዋል።
ባለሞያዎቹ በሽታውን ዓመቱን ሙሉ እንደ አደገኛ አደጋ ሊመለከቱት እንደሚገባ አርቢዎችን አስጠንቅቀዋል።
በሽታው በበጋ ሙቀት ወይም በክረምት ቅዝቃዜ ሳይሸነፍ በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በእስያ እና በአፍሪካ ተከስቷል።
የአርጀንቲና እና ኡራጓይ ባለሥልጣናት የመጀመሪያ የበሽታውን መግባት ካረጋገጡ በኋላ የድንገተኛ አደጋ አውጀዋል።
የእንቁላል ዋጋ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በሽታው በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶሮዎችን ጠራርጎ ካጠፋ በኋላ ክብረ-ወሰን ተመዝግቧል ነው የተባለው።
ይህም ዋነኛና እርካሽ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው እንቁላል ለዝቅተኛው የዓለማችን ማህበረሰብ እንዳይዳረስ አድርጓል ተብሏል።ተ
በባለሙያዎች እንደተናገሩት የዱር አእዋፍ በዋነኛነት ለቫይረሱ መስፋፋት ተጠያቂ ናቸው።