የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ማሸነፍ ለቢትኮይን ዋጋ መናር ትልቁ ምክንት ነው ተብሏል
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 94 ሺህ ዶላር ደረሰ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከሶስት ሳምንት በፊት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከሶስት ዓመት በፊት ስለ ቢትኮይን በሰጡት አስተያየት ቢትኮይን የማጭበርበሪያ ስልት ነው ብለው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ዋነኛ የቢትኮይን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የቢትኮይን ደጋፊ መሆናቸውን በይፋ የተናገሩት ትራምፕ ለምርጫ ቅስቀሳቸው ሳይቀር የቢትኮይን ልገሳዎችን ተቀብለዋል፡፡
ይህ ተከትሎም እንደ ቢትኮይን አይነት የምናባዊ መገበያያ ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያዎች ዋጋቸው እየጨመረ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ94 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ወደ 100 ሺህ ዶላር ሊያድግ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
አብዛኛው አክስዮን በዶናልድ ትራምፕ የተያዘው ትሩዝ ሶሻል የተሰኘው የማህበራዎ ትስስር ኩባንያ ባክት የተሰኘውን የክሪፕቶከረንሲ ለመግዛት በድርድር ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ የ10 ሺህ ዶላር ጭማሪ አሳየ
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የዓለም ቢትኮይን ግብይት ማዕከል የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እንደ ቢትኮይን አይነት ግብይቶችን ለማበረታታት የግብር ቅናሽ እና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡
ጥር አጋማሽ ለይ ስራ እንደሚጀመር የሚጠበቀው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር የካቢኔ አባላት መረጣው እንደቀጠለ ሲሆን ኢለን መስክን ጨምሮ እንደሚሾሙ የሚጠበቁት ሀላፊዎች የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይቶችን የሚደግፉ ናቸው፡፡