የመጀመሪያው የቢትኮይን ግብይት ግብይት ፒዛ በመግዛት ተፈጽሟል
የቢትኮይን ዋጋ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ89 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ዋጋው በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል፡፡
የክሪፕቶከረንሲዎች ዋጋ በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ ብቻ የ80 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የቢትኮይን ዋጋ የተያዘው 2024 ዓመት ሳይጠናቀቅ ከ100 ሺህ ዶላር ሊያልፍ እንደሚችል የተለያዩ ግምቶች ተሰጥተዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2017 ላይ አንድ የቢትኮይን ዋጋ 6 ሺህ 200 ዶላር የነበረ ሲሆን በ2021 ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡