በተያዘው ዓመት አንድ ቢትኮይን በ100 ሺህ ዶላር ሊመነዘር እንደሚችል ተገጿል
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ45 ሺህ ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ፡፡
እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ ባለፉት ዓመታት ዋጋው አሽቆልቁሎ የነበረው የዓለም ምናባዊ ወይም ክሊፕቶከረንሲ መገበያያ ገንዘብ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
በዚህ ምክንያት አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ45 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም ከሁለት ዓመታት በኋላ የታየው ከፍተኛ ጭማሪ መሆን ችሏል።
የቢትኮይን ዋጋ በተከታታይ ጭማሪ ያሳየው አሜሪካ በምናባዊ መገበያያ ገንዘብ አክስዮን መሸጥ እና መግዛት እንደሚቻል ከፈቀደች በኋላ ሲሆን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ5 ሺህ ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።
የቢትኮይን ዋጋ ጭማሪ ካሳለፍነው ወር ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ጭማሪ አድርጓል የተባለ ሲሆን ካለፈው ጥር ወር ጋር ሲነጻጸር ደግሞ በ150 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ተገልጿል።
ከሁለት ዓመት በፊት የምናባዊ ወይም ክሪፕዮከረንሲ ግብይቶች ተፈላጊነታቸው መጨመሩን ተከትሎ እስከ 60 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ደርሶም ነበር።
የምናባዊ ገንዘብ ተቀባይነት በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት እየጨመረ ቢመጣም እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ግን እገዳ ጥለዋል።
ኤልሳልቫዶር ቢትኮይን እንደ አንድ የመገበያያ ገንዘብ አድርጋ የተቀበለች ሲሆን ሌሎችም ሀገራት ይህን በመከተል ላይ ይገኛሉ፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም በአሜሪካ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው የምናባዊ ግብይት የጀመሩ ተቋማት ላይ ምርመራ መጀመሩ እና እንደ ሲልከን ቫሊ አይነት ባንኮች ኪሳራ ላይ መውደቃቸው የምናባዊ ግብይት ፍላጎት እያሽቆለቆለ እንዲመጣ ያደረጉ ምክንያቶች ነበሩ።
በነዚህ ምክንያቶችም አንድ ቢትኮይን ከዚህ በፊት ከነበረበት 60 ሺህ ዶላር እስከ 10 ሺህ ዶላር እና በታች ሲመነዘር ቆይቷል።
በኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት የምናባዊ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ እገዳ መጣሉ አይዘነጋም።
ባንኩ አክሎም ምናባዊ ግብይት ያልተፈቀደ እና ህገወጥ መሆኑን ጠቅሶ የዚህ ግብይት ጥቅምና ጉዳት እንዲሁም አሰራሩ ስለሚዘረጋበት ሁኔታ በቀጣይ ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቆም ነበር።
ኢትዮጵያ ቢትኮይንን መሰል የዲጂታል መገበያያ ገንዘቦችን አገደች
ይህ በዚህ እንዳለ ደግሞ የሩሲያው ቢቲሲ የተሰኘው የምናባዊ ገንዘብ ተቋም በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማዕከሉን እንደሚከፍት መግለጹ ይታወሳል፡፡
በያዝነው አዲሱ የፈረንጆች 2024 ዓመት ውስጥ የቢትኮይን ዋጋ የሚጨምርበት ይሆናል የተባለ ሲሆን እስከ አንድ ቢትኮይን 100 ሺህ ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ባለሙያዎች ተንብየዋል፡፡