የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከሶስት ዓመት በኋላ ከ41 ሺህ ሺህ ዶላር በላይ መመንዘር ጀመረ
አሜሪካ ከዓመታት ምርመራ በኋላ በአክስዮን ገበያ ላይ መገበያየት እንዲቻል ፈቀድ ሰጥታለች
ቻይና የቢትኮይን መገበያያን ካገደች በኋላ የምናባዊ መገበያያ ገንዘብ ለዓመታት አሽቆልቁሎ ቆይቷል
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከሶስት ዓመት በኋላ ከ41 ሺህ ሺህ ዶላር በላይ መመንዘር ጀመረ።
እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ የዓለም ምናባዊ ወይም ክሊፕቶከረንሲ መገበያያ ገንዘብ ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
በዚህ ምክንያት አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ41 ሺህ 522 ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም ከዓመታት በኋላ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
የቢትኮይን ዋጋ ጭማሪ ያሳየው አሜሪካ በምናባዊ መገበያያ ገንዘብ አክስዮን መሸጥ እና መግዛት እንደሚቻል ከፈቀደች በኋላ ነው።
የቢትኮይን ዋጋ ጭማሪ ካሳለፍነው ወር ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ጭማሪ አድርጓል የተባለ ሲሆን ካለፈው ጥር ወር ጋር ሲነጻጸር ደግሞ በ150 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ተገልጿል።
ከሁለት ዓመት በፊት የምናባዊ ወይም ክሪፕዮከረንሲ ግብይቶች ተፈላጊነታቸው መጨመሩን ተከትሎ እስከ 60 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ደርሰው ነበር።
የምናባዊ ገንዘብ ተቀባይነት በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት እየጨመረ ቢመጣም እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ግን እገዳ ጥለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለም በአሜሪካ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው የምናባዊ ግብይት የጀመሩ ተቋማት ላይ ምርመራ መጀመሩ እና እንደ ሲልከን ቫሊ አይነት ባንኮች ኪሳራ ላይ መውደቃቸው የምናባዊ ግብይት ፍላጎት እያሽቆለቆለ እንዲመጣ ያደረጉ ምክንያቶች ነበሩ።
በነዚህ ምክንያቶችም አንድ ቢትኮይን ከዚህ በፊት ከነበረበት 60 ሺህ ዶላር እስከ 10 ሺህ ዶላር እና በታች ሲመነዘር ቆይቷል።
እንደ ሲኤን ኤን ዘገባ ደግሞ አሁን ላይ በርካታ የዓለም የቢዝነስ ድርጅቶች ምናባዊ ገንዘብ የመጠቀም ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ የምናባዊ ገንዘብ ምንዛሬ እንዲያድግ ማድረጉ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት የምናባዊ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ እገዳ መጣሉ አይዘነጋም።
ባንኩ አክሎም ምናባዊ ግብይት ያልተፈቀደ እና ህገወጥ መሆኑን ጠቅሶ የዚህ ግብይት ጥቅምና ጉዳት እንዲሁም አሰራሩ ስለሚዘረጋበት ሁኔታ በቀጣይ ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቆም ነበር።