“ትሸታላችሁ”ተብለው ከአውሮፕላን በረራ ላይ እንዲወርዱ የተደረጉ መንገደኞች ክስ መሰረቱ
መንገደኞቹ በበረራ አስተናጋጅ ከተቀመጡበት ወንበር እንዲወርዱ ተደርገዋል ተብሏል
ክስ የተመሰረተበት የአሜሪካን አየር መንገድ ጉዳዩን እንደሚመረምር አስታውቋል
“ትሸታላችሁ”ተብለው ከአውሮፕላን በረራ ላይ እንዲወርዱ የተደረጉ መንገደኞች ክስ መሰረቱ፡፡
ከፎኒክስ አሪዞና ወደ ኒዮርክ ለመጓዝ ወንበራቸው ላይ የነበሩ ጥቁር አሜሪካዊያን በበረራ አስተናጋጅ አማካኝነት ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ይነገራቸዋል፡፡
የበረራ አስተናጋጁ ጥቁር አሜሪካዊያንን መርጦ ለምን እንዳስወረዳቸው ሲጠየቅም ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ መጥፎ ሽታ ያለው መንገደኛ በመኖሩ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል ተብሏል፡፡
በተለያዩ ወንበሮች ላይ የተቀመጡት እና የማይተዋወቁት እነዚህ አምስት ጥቁር አሜሪካዊያን መጥፎ የሰውነት ሽታ አለ በሚል ከየተቀመጥንበት ተመርጠን እንድንወርድ መደረጋችን ግልጽ ዘረኝነት ነው ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
እስራኤል በሀማስ ላይ "ሙሉ ድል" ትቀዳጃለች ብለው እንደማያምኑ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናገሩ
በመጨረሻም በረራው ቢዘገይም በዚሁ አውሮፕላን አብረው እንዲጓዙ ከተደረጉ አምስት ጥቁር አሜሪካዊያን መካከል ሶስቱ ክስ መስርተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ለደረሰብን የዘረኝነት ጥቃት አየር መንገዱ ካሳ ሊከፍለን ይገባል ሲሉ ክስ የመሰረቱት እነዚህ ሶት አሜሪካዊያን በተፈጠረው ክስተት ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡
ክስ የቀረበበት የአሜሪካን አየር መንገድ በበኩሉ በመንገደኞቹ ላይ የተፈጸመው ዘረኝነት እና መድሎ መሆኑን አስታውቋል፡፡
መንገደኞችን እንደማያበላልጥ እና መድሎን እንደማይከተል ገልጾ የተፈጠረውን ክስተት እንደሚጣራም አየር መንገዱ ገልጿል፡፡
በፈረንጆቹ 2017 ላይ አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጥቁር አሜሪካዊያን ዘረኝነት እና መድሎዎችን ለመራቅ በአሜሪካን አየር መንገዶች እንዳይበሩ ሲል አስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን አየር መንገዶች ማስተካከያ አድርገናል ማለታቸውን ተከትሎ ማስጠንቀቂያውን አንስቷል፡፡