የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በመበጠሳቸው ምክንያት በሶስት ክልሎች የኃይል መቋረጥ አጋጠመ
ኤሌክትሪክ ኃይል እንደገለጸው በኃይል ማስተላላፊያ መስመሮች ላይ የመበጠስ አደጋ ያጋጠመው በነፋስ መውጫ እና በሽዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ ነው
በሁለት ቦታዎች በሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ባጋጠመው የመበጠስ አደጋ መጠነሰፊ የኃይል አቅርቦት መቋረጥ መከሰቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በመበጠሳቸው ምክንያት በሶስት ክልሎች የኃይል መቋረጥ አጋጠመ።
በሁለት ቦታዎች በሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ባጋጠመው የመበጠስ አደጋ መጠነሰፊ የኃይል አቅርቦት መቋረጥ መከሰቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
በኤሌክትሪክ ኃይል በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ ባጋጠመው የማስተላለፋያ መስመር መበጠስ ምክንያት በአማራ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልል ያሉ በርካታ ከተሞች የኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል ብለዋል።
ኤሌክትሪክ ኃይል እንደገለጸው በኃይል ማስተላላፊያ መስመሮች ላይ የመበጠስ አደጋ ያጋጠመው በነፋስ መውጫ እና በሽዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ ነው።
ከባህር ዳር- ደብረታቦር-ንፋስመውጫ-የተዘረጋው 230 ቮልት የተሸከመው ማስተላለፊያ መስመር አንጀኛው ፌዝ በዛሬው እለት በመበጠሱ በርካታ ከተሞች ኃይል አልባ ሆነዋል ብሏል ኤሌክትሪክ ኃይል።
ሸዋሮቢት አካባቢ በተፈጠረው የመበጠስ አደጋ ደግሞ ከሽዋ ሮቢት እና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር በአብዛኛው የሰሜን ምክራቅ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት መቋረጡን ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል።
ከከቦምልቻ በባቲ አቅጣጫ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል ዋና ከተማን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ወረዳዎች ኃይል ተቋርጦባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከወልዲያ አላማጣ በተዘረጋው መስመር የኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ እና በርካታ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው በመግለጫው ጠቅሷል።
ኤልክትሪክ ኃይል አገልግሎቱን ለመመለስ ጥረት እያደረግሁ ነው ብሏል።