አሜሪካ በጋዛ ጉዳይ የአረብ ሀገራት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች
ብሊንከን "አሁን ላይ ተኩስ አቁም የሚደረግ ከሆነ ሀማስ ወደ ቦታው እንዲመለስ እና የጥቅምት 7ቱን ጥቃት እንዲደግሙ ማስቻል ነው።" ብለዋል
ብሊንከን በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ግፊት የሚያደርጉትን የአረብ ሀገራት አልተቀበሏቸውም
አሜሪካ በጋዛ ጉዳይ የአረብ ሀገራት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ግፊት የሚያደርጉትን የአረብ ሀገራት አልተቀበሏቸውም።
ፍልስጤም በተመድ በሚተዳደረው ትምህርት ቤት ውስጥ 15 ሰዎች መገደላቸውን ከገለጸች ከሰአታት በኋላ የአረብ መሪዎች በትናንትናው እለት በጋዛ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በብሊንከን ላይ በግልጽ ጫና አሳድረዋል።
አለመስማማታቸውን ባልተለመደ መልኩ በአደባባይ የገለጹት ብሊንከን ተኩስ አቁም ሀማስ መልሶ እንዲደራጅ እድል ይፈጥረታል ብለዋል።
አራት ሳምንታት ያስቆጠሰውን የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እንዴት ማርገብ እንደሚቻል የቀጣናው እና የአለም መሪዎች ስምምነት ላይ አልደረሱም።
የጥቅምቱን የሀማስ ጥቃት ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች ያለችው እስራኤል አሁን ላይ በጋዛ ውስጥ ውጊያ እያካሄደች ትገኛለች።
ብሊንከን በጋዛ ጉዳይ ከሳኡዲ፣ ከጆርዳን፣ ከአረብ ኢምሬትስ እና ከግብጽ ጋር መክረዋል።
የጆርዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "አሁን የምንፈልገው ይህ ተኩስ እንዲቆም ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ብሊንከን ግን በዚህ አይስማሙም።
በጋዛ አሁን ያለው ሁኔታ መቀጠል የለበትም በሚለው ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን የገለጹት ብሊንከን ልዩነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ብሊንከን "አሁን ላይ ተኩስ አቁም የሚደረግ ከሆነ ሀማስ ወደ ቦታው እንዲመለስ እና የጥቅምት 7ቱን ጥቃት እንዲደግሙ ማስቻል ነው።" ብለዋል።
እስራኤል በአየር፣ በባህር እና በአየር እየሰነዘረች ባለው ጥቃት ምክንያት የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ከፍተኛ የሚባል የሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል።
በጥቃቱ እስካሁን 9488 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የተመድ ባለሙያዎች በጋዛ የዘርማጥፋት አደጋ አንዣቧል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።