ብሊንከን ሳኡዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር በምታደርገው ግንኙነት የማደስ ንግግር ጉዳይ መሻሻል መኖሩን ተናገሩ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፍልስጤም እንደሀገር መቋቋምን በተደጋጋሚ ውደቅ አድርገዋል።
አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ፣ በሳኡዲ እና እሰራኤል መካከል ባለው ግንኙነት የማደስ ሂደት ንግግር ላይ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ብሊንከን ተናግረዋል
ብሊንከን ሳኡዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር በምታደርገው ግንኙነት የማደስ ንግግር ጉዳይ መሻሻል መኖሩን ተናገሩ።
አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ፣ በሳኡዲ እና እሰራኤል መካከል ባለው ግንኙነት የማደስ ሂደት ንግግር ላይ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ነገርግን ብሊንከን ንግግሩ መቼ እንደሚቋጭ ቀነገደብ አላስቀመጡም።
ብሊንከን በግብጽ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቻቸው ሳሜህ ሻኩሪ ጋር በሰጡት መግለጫ "ለሁለቱ ሀገራት ብሎም ለቀጠናው ታሪካዊ እድል የሚፈጥር ስምምነት ላይ እንደርሳለን ብዬ አምናሉሁ"ብለዋል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተነሳው ግጭት በሁለት ሀገራት መካከል በነበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት የማደስ ንግግር ላይ ቀዝቃዛ ውሃ አፍስሶበታል።
ነገርግን ንግግሩ በድጋሚ በቅርቡ ተጀምሯል።
የፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በጥብቅ ይፈልጋል። ሳኡዲ አረቢያ እና ሌሎች የአረብ ሀገራት ከእሰራኤል ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር ፍልስጤም እንደሀገር መቋቋም አለባት የሚል አቋም እንዳላቸው ሲገልጹ ቆይተዋል።
ሳኡዲ አረቢያ ለምታከናውነው የሲቪል ኑክሌር ፕሮግራም አሜሪካ ድጋፏን እንድትቸራት የሚያስችል ወታደራዊ ስምምነት ላይ መድረስ ትፈልጋለች።
በዚህ ጉዳይ ብሊንከን በረቡዕ በጂዳ ጉብኝታቸው ከሳኡዲው ልኡል አልጋ ወራሽ መራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር መክረውበታል ተብሏል።
አሜሪካ ለሳኡዲ አረቢያ ወታደራዋ ድጋፍ ለማድረግ የምትስማማ ከሆነ እና ሳኡዲም በምትኩ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን የምታድስ ከሆነ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኞችን አንድ በማድረግ የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናን ይቀይረዋል ተብሏል።
ይህ እንዲሳካ ግን እስራኤል የፍልስጤምን እንደሀገር መቋቋም ልትፈቅድ ይገባል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፍልስጤም እንደሀገር መቋቋምን በተደጋጋሚ ውደቅ ማድረጓ ይታወሳል።