የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይና ሩሲያን እንዳትረዳ አስጠነቀቁ
ዋሽንግተን ቻይና ለሩሲያ ድጋፍ ለማድረግ እያሰበች መሆኗ አሳስቦኛል ብላለች
ሞስኮና ቤጂንግ "ገደብ የለሽ" የአጋርነት ስምምነት ከጦርነቱ አስቀድሞ ተፈራርመዋል
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የቻይና ከፍተኛውን ዲፕሎማት ዋንግ ዪን ቤጂንግ ለሩሲያ የቁሳቁስ ድጋፍ ብታደርግ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል ተብሏል።
የሁለቱ ሀያላን ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በሙኒክ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ጉባኤ ላይ ተገናኝተው መምከራቸው ተነግሯል።
- ሰላይ ናቸው የተባሉት ፊኛዎች ጉዳይ የአሜሪካ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫን
- እያባባሰ ነው ተባለ
- ቻይና በአየር ክልሏ ላይ አሜሪካ ከፍተኛ ከፍታ ያላቸው ፊኛዎችን አብራለች ስትል ወቀሰች
ውይይቱ የተካሄደው በሚስጥርና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ "የቻይና ሰላይ ፊኛ" አሜሪካ መውደቁን ተከትሎ በተነሳ ውዝግብ በኋላ ነው።
ውዝግቡ የመጣው ምዕራባውያን ቤጂንግ ለሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የምትሰጠውን ምላሽ በቅርበት በሚከታተሉበት ወቅት መሆኑን ሮይተርስ ጠቅሷል።
ብሊንከን በኤንቢሲ ዜና ላይ ቀርበው ሀገራቸው ቻይና ለሩሲያ ድጋፍ ለማድረግ እያሰበች መሆኗ በጣም እንዳሳሰባት እና ለዋንግ ይህን ግልጽ አድርገናል ብለዋል።
"ገዳይ የጦር መሳሪያን ጨምሮ ለማቅረብ እያሰቡ ያሉት የተለያዩ አይነት እርዳታዎች አሉ" ያሉት ብሊንከን በቅርቡ ዋሽንግተን ተጨማሪ ዝርዝሮችን እንደምትሰጥ ተናግረዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በሰጠው አጭር መግለጫ ዋንግ ለብሊንከን አሜሪካ “በአድልዎ የኃይል አጠቃቀም ምክንያት የተፈጠረውን መቃቃር ለመፍታት ወደ ኋላ ማለት የለባትም” ማለታቸውን ጠቅሷል።
በቅርቡ ውዝግብ ያስነሳው "የስለላ ፊኛ" ውጥረት ላይ የነበረውን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንዲካረር አድርጓል እየተባለ ነው።
የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ሞስኮና ቤጂንግ " ገደብ የለሽ" አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።