ቻይና ፤ በአሜሪካ ሰማይ ላይ ታይተዋል ስለተባሉት “ሰላይ ፊኛዎች” የማውቀው ነገር የለም አለች
ፔንታጎን፤ኤፍ-16 ተዋጊ ጄትን በመጠቀም ፊኛውን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል
የፊኛው ጉዳይ የዋሽንግተን-ቤጂንግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ይበልጥ የሚያሻክር ሊሆን እንደሚችል ይገመታል
ቻይና ፤ በአሜሪካ ሰማይ ላይ ታይተዋል ስለተባሉት “ሰላይ ፊኛዎች” የማውቀው ነገር የለም አለች።
ቻይና ከሰሞኑ በአሜሪካ ተመትቶ እንዲወድቅ የተደረገውና በስላላ የተጠረጠረው የቻይና ፊኛ ዙሪያ የመጀመያ አስተያየት ሰጠች፡፡
የፔንታጎን መረጃ እንደሚያመክተው ከሆነ፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትእዛዝ ካስተላለፉ በኋላ በአሜሪካ እና በካናዳ ድንበር ላይ ባለ የአየር ክልል ላይ የነበረውን ፊኛ ተመትቶ ወድቋል፡፡
አሜሪካ የአየር ክልሏን የጣሱትን እንደዚህ አይነት ፊኛ መሳይ ቅርጽ ያላቸው ተማሳሳይ ነገሮች መትታ ስታወድቅ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ እንደሆነም የተገለጸው፡፡
የአሜሪካ ጦር የአሁኑ ፊኛውን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ለመጣል ኤፍ-16 ተዋጊ ጄት ተጠቅሟልም ተብሏል፡፡
ዋሽንግተን የቤጂንግ ነው የምትለውንና ተምትቶ የወደቀው ፊኛ መረጃዎችን የመሰብሰብ አቅም እንዳለውም ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
ፊኛው በአብዛናው የዓለም ክፍል መጠነ ሰፊ ስለላ ስራ ማከናወን የሚያስችል ይዘት ያለው እንደሆነም ነው አሜሪካ የገለጸችው፡፡
“በርካታ የስለላ ሴንሰሮች” የተገጠሙለትና 60 ሜትር ያህል ቁመት ያለው ፊኛ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን ቦታ መለየት የሚችል መሆኑም ጭምር ይነገርለታል፡፡
ይሁን እንጅ ሰላይ ናቸው ከተባለው ፊኛዎች ጋር በተገናኘ ስሟ እየተነሳ ያለው ቤጂንግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል በሰጠችው መግለጫ በዋሽንግተን በኩል የሚቀርበውን ክስ ውድቅ አድርጋለች፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ፤ “ቤጂንግ ስለእነዚያ በአሜሪካ እና ካናዳ ተመትተው ወደቁ ስለተባሉና ከቻይና ጋር እየተያያዙ ስለሚነሱት ፊኛዎች ምንም አይነት መረጃ የላትም” ብሏል፡
ቻይና ከእነዚህ በሰሜን አሜሪካ ሰማይ ላይ ከታዩት ፊኛዎች ጋር ያላትን ግንኙነት ብትክድም ፤ ቤጂንግ አሁን ላይ ለቴክኖሎጂ እየሰጠች ባለው ልዩ ትኩረት እንደ አሜሪካ ባሉ ሌሎች ሀገራት “ጠፈር” የምትለውን ለመቆጣጠር ጥረት ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ስለዚህም ቻይና ፊኛ የሚመስሉና “የስልላ ስራ ለማከናወን” የሚያስችሉ በርካታ አንቴናዎች ያሏቸው ነገሮች ልትሰራ ትችላለችም ነው የተባለው፡፡
ይህ ብእንዲህ እንዳለ የፊኛው ጉዳይ የዋሽንግተን-ቤጂንግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ይበልጥ የሚያሻክር እንደሚሆን እየተገጸ ነው፡፡
ወደ ቻይና ሊደረግ ታስቦ ነበረው የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት አንቶኒ ብሊንክን ጉብኝት መሰረዙም የዚሁ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡