የትዊትር ወይም ኤክስ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆኖ የመጣው ብሉስካይ ማን ነው?
ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድርን ለመቀላቀል መወሰኑን ተከትሎ ብሉ ስካይን የሚቀላቀሉ ደንበኞች በርክተዋል
ከአሜሪካ ምርጫ በኋላ ብሉ ስካይ ከ2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አፍርቷል
የትዊትር ወይም ኤክስ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆኖ የመጣው ብሉስካይ ማን ነው?
ባሳለፍነው ሳምንት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተደርገው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ መንግስታቸውን ለማቋቋም በሂደት ላይ ሲሆኑ የሚሾሟቸውን ሰዎች እያዘጋጁ ናቸው፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድርን እንዲቀላቀሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ በይፋ ተቀብለዋል፡፡
በቀድሞ ስሙ ትዊትር አሁን ለይ አክስ ተብሎ የሚጠራውን የማህበራዊ ትስስር ገጽን የገዙት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕን አስተዳድር እቀላቀላለሁ ካሉ እና ከምርጫው በኋላ ኤክስን የሚለቁ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡
በቀድሞ የትዊተር መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጃክ ዶርሴይ የተመሰረተው ብሉስካይ መተግበሪያ የኤክስ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆኖ መጥቷል፡፡
ከዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት 13 ሚሊዮን ደንበኞች የነበሩት ብሉ ስካይ አሁን ላይ በጎግል ፕሌይ እና አፕ ስቶር ላይ ብዙ ተጠቃሚ ካገኙ መተግበሪያዎች መካከል የመጀመሪያው መሆን ችሏል፡፡
አሁን ላይ ከ16 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ የተገለጸው ብሉ ስካይ በተጠቃሚዎች ብዛት መተግበሪያው በመጨናነቅ ለይ እንደሆነ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሰዎች ከኤክስ ይልቅ ወደ ብሉስካይ ያዘነበሉት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድርን በመቀላቀሉ ምክንያት ነው፡፡
ከግለሰቦች በተጨማሪም እንደ ዘ ጋሪዲያን ያሉ ሚዲያዎች ሳይቀር ኤክስን መጠቀም ያቆሙ ሲሆን ምክንያታቸው ደግሞ ከገለልተኝነት ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል፡፡
የብሉ ስካይ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ጃክ ዶርሴይ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለኢለን መስክ በ2019 መሸጡ ይታወሳል፡፡