ልዩልዩ
በቱኒዝያ ስደተኞችን የያዘች ጀልባ መስጠሟን ተከትሎ የ43 ስደተኞች ሕይወት አለፈ
ጀልባዋ ከኤርትራ፣ ግብፅ፣ ሱዳንና ባንግላዴሽ የነተሱ ስደተኞችን ጭና ነበረ
ሌሎች 84 ስደተኞች በተኒዚያ ባሕር ኃይል አባላት እገዛ ከመስመጥ አደጋ ሊተርፉ ችለዋል
በቱኒዝያ ስተደኞችን የያዘች ጀልባ ሰጥማ የ43 ስተኞች ህይወት ማፉን የቱኒዚያ ቀይ ጨረቃ ማሕበር አስታወቀ።
ስደተኞቹ ከሊቢያዋ የዙዋራ ወደብ ተነስተው የሜዲቲራኒያን ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ በመሄድ ላይ የነበሩ ናቸውም ነው የተባለው፡፡
ጀልባዋ ጉዞ የጀመረችው ሰኞ ምሽት ሲሆን፤ በውስጧ ከግብፅ፣ ሱዳን፣ ኤርትራና ባንግላዴሽ የመጡ ስደተኞችን ይዛ ነበር፡፡
በጀልባዋ ላይ የነበሩ ሌሎች 84 ሰዎች በተኒዚያ ባሕር ኃይል አባላት እገዛ ከመስጠም እንደተረፉም የቱኒዚያ ቀይ ጨረቃ ማሕበር ኃላፊ ሞንጊ ስሊም ተናግረዋል።
ስደተኞችን ጭና ስትጓ የነበረችው ጀልባ በጋጠማት የሞተር ችግር ምክንያት በባሀር መሃል ላይ የመስጠም አደጋ እንዳጋጠማትም ነው የቱኒዚያ ቀይ ጨረቃ ማሕበር ያስታወቀው።
የቱኒዚያ መከላከያ ሚኒስቴር ከቱኒዚያዋ የዛርዚስ ወደብ በሕይወት ተርፈው የተገኙት ስደተኞች ዕድሜያቸው ከሶስት እስከ 40 ዓመት መካከል መሆኑንም አስታውቋል።
ሊቢያ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚፈልጉ ስደተኞች ትልቋ መዳረሻ ናት።
ነገር ግን ቱኒዚያም ሌላኛዋ ከአፍሪካ ሃገራት ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚሹ ስደተኞች መሻገሪያ ሃገር ሆናለች።