የቦይንግ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቭ ካልሆን ኃላፊነታቸውን ሊለቁ መሆኑን ኩባንያው አስታወቀ
ካልሆን የአላስካ አየርመንገድ የሆነ ቦይንግ አውሮፕላን በ16ሺ ጫማ ከፍታ ላይ እያለ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ መከፈቱን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተው ቆይተዋል።
የቦይንግ ኩባንያ ቦርድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ እያለ ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ እየወሰደ ባለው የአመራር ለውጥ ዋና ስራ አስፈጻሚው ዴቭ ካልሆን ሊነሱ ነው
የቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቭ ካልሆን ኃላፊነታቸውን ሊለቁ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።
የግዙፍ ከውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ ቦርድ ባለፈው ጥር ወር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ እያለ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ መከፈቱን ተከትሎ እየወሰደ ባለው የአመራር ለውጥ ዋና ስራ አስፈጻሚው ዴቭ ካልሆን በአመቱ መጨረሻ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በተጨማሪም የቦይንግ ኮመርሻል አውሮፕላን ፕሬዝደንት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ስታን ዲል ጡረታ እንደሚወጡ እና ስቴፋኒ ፖፕ እንደሚተኳቸው ኩባንያው ገልጿል።
ካልሆን ባለፈው ጥር ንብረትነቱ የአላስካ አየርመንገድ የሆነ ቦይንግ አውሮፕላን በ16ሺ ጫማ ከፍታ ላይ እያለ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ መከፈቱን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተው ቆይተዋል።
ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ አየርመንገደች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የአላስካ አየርመንገድ አውሮፕላን ካጋጠመው ችግር በተያያዘ ያላቸዉን ስጋት ለመግለጽ የቦይንግ ዳይሬክተሮችን ለማናገር ፈልገው ነበር።ይህ በኩባንያው እና ካልሆን የመደናገጥ ሰሜት እንዲፈጠርባቸው አድርጓል።
ኩባንያው የቀድሞውን ስብሲዲያሪውን ስፕሪት ኤሮ ሲስተምን ለመግዛት እየተነጋገረ ነው።
ትዕዛዝ በፍጥነት ባለማድረስ ቀውስ ውስጥ የገባው ኩባንያው አየርመንገዶችን ተስፋ እያስቆረጣቸው እንደሚገኝ እና በዚህ ሩብ አመት ከተጠበቀው በላይ ወጭ ማውጣቱ ተገልጿል።
የቦይንግ ዋነኛ ተቀናቃኙ ኤየር ባስ፣ የቦይንግ ቁልፍ የእስያ ደንበኞች ከነበሩት ጋር 65 አውሮፕላን ለማምረት ውል አስሯል። ይህ የአየር መንገድ ኃላፊት በቦይንግ ላይ ስጋት እንዳደረባቸው የሚያሳይ ነው ተብሏል።