ድርጅቱ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን እንዳያመርት የታገደ ሲሆን የደረሰበትን የቴክኒክ ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ወጪ ለማውጣት ተገዷል
ቦይንግ ኩባንያ በሶስት ወራት ውስጥ የ4 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደረሰበት፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ አቪዬሽን ኩባንያ የሆነው የአሜሪካው ቦይንግ የ737 ማክስ የተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ ችግሮች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ደንበኞቹን እና የገንዘብ ኪሳራዎችን በማስተናገድ ላይ ነው፡፡
የአሜሪካ ፌደራል ባለስልጣንም ቦይንግ ኩባንያ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን እንዳያመርት ከሁለት ወር በፊት ጊዚያዊ እገዳ መጣሉ አይዘነጋም፡፡
ባለስልጣኑ በቦይንግ ላይ የጣለው ጊዜያዊ እገዳ ንብረትነቱ የአላስካ እና ዩናይትድ አየር መንገዶች የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ መስኮቱ መገንጠሉን ተከትሎ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል።
ድርጅቱ በ737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የቴክኒክ ችግሮች መከሰቱን ተከትሎ አውሮፕላኖቹ ከበረራ የታገዱ ሲሆን ኩባንያው ይህን ችግሩን ለመፍታት 4 ቢሊዮን ዶላር ካሽ ወጪ ለማድረግ ተገዷል ተብሏል፡፡
ቦይንግ ኩባንያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ከበረራ በመታገዳቸው ምክንያት 355 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ድርጅቱ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ የደረሰውን የቴክኒክ ችግሮችን ለመፍታት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉንም ገልጿል፡፡
ኩባንያው ባጋጠሙት የአውሮፕላን ምርቶች ምክንያት የማክስ 737 አውሮፕላን ምርት ክፍል ሀላፊ ኢድ ክላርክን ከአንድ ወር በፊት ከሀላፊነት ማንሳቱን ይታወሳል፡፡
የቦይንግ ኩባንያ ሚስጢሮችን ያጋለጠው ሰው ሞቶ ተገኘ
ኢድ ክላርክ ቦይንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ 171 ማክስ 737 አውሮፕላኖች ከበረራ እንዲታገዱ ምክንያት ሆኗል በሚል ከሀላፊነት እንዳነሳቸው በወቅቱ ይፋ አድርጎ ነበር፡፡
የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላን ምርት ጋር በተያያዘ የቴክኒክ ችግሮች ማጋጠሙን ተከትሎ የአክስዮን ዋጋው ከመቀነሱ በተጨማሪ ከተቋማት ይቀርብለት የነበረው የአውሮፕላን ግዢ ቁጥርም እንዲቀንስ ምክንት ሆኗል፡፡
የቦይንግ ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆነው ኤርባስ ኩባንያ ገበያ እንደደራለት ሲገለጽ የአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን ቦይንግ ያሉበትን የቴክኒክ ችግሮች እንዲፈታ አጭር ጊዜ መስጠቱ ተገልጿል፡፡