የቦይንግ አውሮፕላን የሞተር ሽፋን በበረራ ላይ ተገንጥሎ መውደቁን ተገለጸ
ወደ ሁስቶን ሲጓዝ የነበረው የሳውዝዌስት አየር መንገድ አውሮፕላን ዴንቨር ለማረፍ ተገዷል
135 መንገደኞችንና 6 የበረራ አባላት ያሳፈረው አውሮፕላን 10 ሺህ 300 ጨማ ከፍታ ላይ እየበረረ ነበር
የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ የሞተሩ ሽፋን ተገንጥሎ መውደቁ ተነገረ።
ወደ አሜሪካዋ ሁስቶን በረራ ላይ የነበረው አውሮፕላ ቸግሩ ማገገሙን ተከትሎ ዴንቨር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱ ተነግሯል።
135 መንገደኞችንና 6 የበረራ አባላት ያሳፈረው አውሮፕላን ዴንቨር ለማረፍ ከመደገጉ በፊት 10 ሺህ 300 ጨማ ከፍታ ላይ እየበረረ እንደነበረም ነው የተገለጸው።
ችግሩ ማጋጠሙን ተከትሎ የአሜሪካ የአየር መንግድ ተቆጣጣሪዎች አፋጣኝ ምርመራ እያደረጉ መሆኑም ተነግሯል።
የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ያጋጠመውን ችግር የአየር መንገዱ የጥገና ቡድን እንደሚመረምረው አስታውቀዋል።
አየር መንገዱ ለእንደዚህ አይነት ክፍሎች ጥገና ኃላፊነት እንዳለበት አረጋግጧል።
ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን የተመረተው በፈረንጆቹ በ2015 መሆኑን የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) መረጃ ያመለክታል።
ቦይንግ ኩባንያ የአሜሪካው የሳውዝዌስት አየር መንገድ በቦይንግ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ ባጋጠመው ችግር ዙሪያ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።
የዓለማችን ግዙፍ የአቪየሽን ኩባንያ የሆነው ቦይንግ ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ በ737 ማክስ 9 አውሮፕላን መስኮቱ ተገንጥሎ መውደቁን ተከትሎ ትችቶችን እያስተናገደ ይገኛል።
ከዚህ ጊዜ በኋላ ተደጋጋሚ የምርት ጥራት ችግሮች የተከሰቱ ሲሆን የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳድር በኩባንያው ላይ የቴክኒክ ጥራት ምርመራዎችን አድርጓል።
ኩባንያው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርቶች ላይ ካከናወናቸው 89 የጥራት ምርመራዎች ላይ በ33ቱ ጉድለት እንደተገኘበት መገለጹም ይታወሳል።
ይህ አውሮፕላን በተለይም የኤሮ ሲስተሙ ሲፈተሸ የጥራት ደረጃውን ያሟላው ከ13 ነጥቦች በስድስቱ ብቻ አልፏል ተብሏል።
የኩባንያው የቴክኒክ ባለሙያዎች ስለ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በቂ እውቀት እንዳላቸው በተደረገው ምርመራ የሚገባውን ያህል ያውቃሉ የሚለውን ኩባንያው ማስረዳት እንዳልቻለም ተገልጿል።