ከኖርዌይ ፖላር ኢንስቲትዩት የተውጣጡ 45 ተመራማሪያዎች እና ሰራተኞችን የያዘው ቡድን 12 ቶን የሚመዝን የምርምር ቁሳቁሶችን ማምጣት መቻሉ ተገልጿል
300 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ቦይንግ 787 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንታርቲካ ማረፍ ችሏል።
የሳይንቲስቶችን ቡድን የያዘው አውሮፕላን በአንታርቲካ ማረፍ መቻሉን በበረራ ዘረፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ማድነቃቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
አውሮፕላኑ ያረፈው 'ትሮል' በተባለው አየርመንገድ ባለፈው ሮብዕ ነበር።
ከኖርዌይ ፖላር ኢንስቲትዩት የተውጣጡ 45 ተመራማሪያዎች እና ሰራተኞችን የያዘው ጠንካራ ቡድን 12 ቶን የሚመዝን የምርምር ቁሳቁሶችን ማምጣት መቻሉ ተገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ ዳይክተር ካሚላ ብሬክ ይህ ትልቅ ዘመቻ ወደ 'ኩይን ሙአድ ላንድ' ለሚደረገው በረራ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዳይሬክሩ እንደገለጹት ትላልቅ አውሮፕላኖችን በትሮል ማሳረፍ መቻሉ የኖርዎይን የአንታርቲካ ምርምር ያጠናክረዋል።
የትሮሎ አየርመኔገድ 3000 ሜትር የሚረዝም ሲሆን ክረምት ከመግባቱ በፊት ከጥቅምት እስከ ሚያዝያ ድረስ አገልግሎት ይሰጣል።
አውሮፕላኑን የማሳረፍ ስራው ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ ቢሆንም ለኮመርሻል በረራ ወይም ለመደበኛ የመንገደኞች በረራ ክፍት ስለመደረጉ የተባለ ነገር የለም።