ቦይንግ በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማማ
አውሮፕላኑ የ35 ሀገራት ዜግነት ያላቸው 157 ሰዎች አሳፍሮ ነበር
157 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲጓዝ የነበረው ንብረትንቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ማክስ737 አውሮፕላን ከስድስት ደቂቃዎች በረራ በኋላ መከስከሱ ይታወሳል
መጋቢት 1፤2011ዓ.ም ቢያንስ 157 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲጓዝ የነበረው ንብረትንቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበረራ ቁጥር 302 ቦይንግ ማክስ737 አውሮፕላን ከቦሌ አለምአቀፍ አየር መንገድ ከተነሳ ስድስት ደቂቀዎች በኋላ መከስከሱ ይታወሳል፡፡
ኩባንያው በ737 አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ከጡ ቤተሰቦች ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል፤ለግጭቱም ሃላፊነቱም ወስዷል፡፡
ሮይተርስ እንዘገበው በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች በሙሉና በፍትሃዊ መሆነ መንገድ መካሳቸውን ለማረጋገጥ ለመስራት ቁርጠኛ ነው፡፡
ኃላፊነትን በመውሰድ፤ ኩባንያው ከተጎጆ ቤተሰቦች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ተገቢ የሆነ ክፍያ ለመወሰን በሚያደርገው ጥረት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ያስችለዋል ብለዋል፡፡ የተጎጅ ቤተሰቦች ጠበቃ ሮበርት ክሊፍሮፍድ ስምምነት ታሪካዊ መሆኑን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ተደረስ የተባለው ስምምነት የገንዘቡን መጠን አለመጥቀሱ የተገለጸ ሲሆን ዳኞች በቀረበው መረጃ መሰረት የካሳውን መጠኝ ይገምታሉ ተብሏል፡፡
የቦይንግ 737 የመከስከስ አደጋ፤ የማክስ 737 አውፕላኖች በሙሉ እንዳይበሩ የታገዱበትና በተለይም ንብረትንቱ የኢንዶኔዥያ የሆነው 189 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው ማክስ 737 አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ መከሰቱ በአሜሪካ የበረራ ታሪክ መጥፎ የሚባል ቀውስ ፍጥሮ ነበር፡፡
የተከሰከሰው የኢትዮጵያው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ኢትዮጵያን ጨምሮ የ35 ሀገራት ዜግነት ያላቸው 157 ሰዎች አሳፍሮ እንደነበር ይታወሳል፡