ቦልሴናሮ የብራዚል ምርጫ ሽንፈትን በመቃወም ድምጹ ውድቅ እንዲደረግ እሻለሁ አሉ
በብራዚል ምርጫ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በጠባብ ልዩነት ማሸነፋቸው ይታወሳል
ገለልተኛ ባለሞያዎች ስህተቱ የውጤቱን አስተማማኝነት አይጎዳውም ብለዋል
በድጋሚ ለመመረጥ የተወዳደሩት ጃኢር ቦልሴናሮ ከተሸነፉ ከሦስት ሳምንታት በኋላ የሶፍትዌር ስህተት ተከስቷል በሚል ድምጹ ውድቅ እዲደረግ ጠይቀዋል።
የምርጫ ባለስልጣኑ በአብዛኛዎቹ የብራዚል ኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫ ማሽኖች ላይ የተሰጠውን ድምጽ እንዲሰርዝ የጠየቁት ቦልሴናሮ፤ ምንም እንኳን ገለልተኛ ባለሞያዎች ስህተቱ የውጤቱን አስተማማኝነት አይጎዳውም ቢሉም።
ባለ 33 ገጽ ጥያቄ በቦልሴናሮ ስም ያቀረቡት ጠበቃ ማርሴሎ ደ ቤሳ እንዲህ ያለው እርምጃ 51 በመቶውን ትክክለኛ ድምጽ ማግኘት ያስችላል በማለት በድጋሚ ምርጫ ድል ተሸናፊው ፕሬዚዳንት ያገኛሉ ማለታቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
የብራዚል የምርጫ ባለስልጣን ውጤትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ እና ብዙ የፕሬዚዳንቱ አጋሮች ተቀብለውታል።
የሊበራል ፓርቲ መሪ ቫልዴማር ኮስታ እና በፓርቲው የተቀጠሩ መርማሪ እ.አ.አ ከ2020 በፊት የነበሩትን ማሽኖች ማለትም በጥቅምቱ ምርጫ ጥቅም ላይ ከዋለው አጠቃላይ 59 በመቶ ያህሉ ማሽኖች የግለሰብ መታወቂያ የላቸውም ብለዋል። ይህም ማሽኖቹ ችግር እንዳለባቸው ያሳያል ነው ያሉት። ችግሩ የምርጫውን ውጤት እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍበት ባይናገሩም፤ የማሽኖች ድምጽ እንዲሻር ግን ጠይቀዋል።
የምርጫ ባለስልጣኑ ፓርቲው በ 24 ሰዓታት ውስጥ ቅሬታውን በማስረጃ አያይዞ ካላቀረበ በስተቀር ፍርድ ቤቱ ቅሬታውን እንደማይመለከተው ገልጿል።
ባለሙያዎች ስህተቱ ውጤቱን እንደማይጎዳ ተናግረዋል።
የቦልሴናሮ በዳ ሲልቫ ጋር ከሁለት ነጥብ ያነሰ ሽንፈት ብራዚል በፈረንጆቹ በ1985 ወደ ዲሞክራሲ ከተመለሰች በኋላ በጣም ጠባብ ልዩነት የታየበት ነው ተብሏል።
በርካቶች የቦርሴናሮ ደጋፊዎች ምርጫ ተጭበርብሯል በማለት የብራዚል ጦር ጣልቃ እንዲገባ በመጠየቅ ተቃውሞ አሰምተዋል።