በተሳሳተ የቦምብ ስጋት በራረውን ያቋረጠው አውሮፕላን
አውሮፕላኑ ከሕንዷ ሞምባይ ወደ ጀርመኗ ፍራንክፈርት እየበረረ ነበር
ይህ የመንገደኞች አውሮፕላን የቦምብ ጥቃቱን ለማምለጥ የቻናቸውን 234 መንገደኞች ቱርክ ላይ ለማውረድ ተገዷል
በተሳሳተ የቦምብ ስጋት በራረውን ያቋረጠው አውሮፕላን
የህንዱ ቪስታራ አየር መንገድ በትናንትናው ዕለት 234 መንገደኞችን አሳፍሮ ከህንዷ የንግድ መዲና ሞምባይ ወደ ጀርመኗ ፍራንክፈርት እየበረረ ነበር፡፡
ይሁንና ይህ አውሮፕላን በጉዞ ላይ እያለ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የተጣለ አንድ ወረቀት ሲገኝ ተሳፋሪዎችን አስደንግጧል፡፡
ይህ የተገኘው ወረቀትም በአውሮፕላኑ ውስጥ ቦምብ አብሮ እንደተጫነ የሚገልጽ ሲሆን በበረራ ላይ የነበረው አውሮፕላን ወዲያውኑ ቱርክ ለማረፍ ተገዷል፡፡
የበረራ ቁጥሩ ዩኬ27 የተሰኘው ይህ አውሮፕላን የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ወዲያውኑ በቱርኳ ገጠራማ ከተማ በሆነችው ኢርዙሩም ኤርፖርት አርፏል፡፡
ዩክሬን የምትመካበት ኤፍ-16 አውሮፕላን መከስከሱን ተከትሎ የአየር ኃይል አዛዡ ተባረሩ
ይሁንና የቱርክ ጸጽታ እና ደህንነት ሰዎች በአውሮፕላኑ ላይ ባደረጉት ፍተሻ የተባለው ቦምብ አልተገኘም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኢርዙሩም ኤርፖርትም ይህ የቪስታራ አየር መንገድ ካረፈ በኋላ ሌሎች አውሮፕላኖች እንዳያርፉ እገዳ ጥሎም ነበር፡፡
13 የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 234 መንገደኞችን የጫነው አውሮፕላን ለተጨማሪ ደህንነት በሚል በዚሁ ኤርፖርት ይቆያል የተባለ ሲሆን አየር መንገዱ ተለዋጭ አውሮፕላን ወደ ኡርዙሩም ኤርፖርት እንደሚልክ እና መንገደኞቹን ወደ ፍራንክፈርት እንደሚጓጉዝ አስታውቋል፡፡
ይሁንና እስካሁን ይህን ሐሰተኛ የቦምብ ጥቆማ ማን እንደሰጠው በዘገባው ላይ አልተጠቀሰም፡፡