የብሪታኒያ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጋዜጠኝነት ተቀጥረው ሊሰሩ ነው
ቦሪስ ጆንሰን “GB News” የቴሌቭዥን ጣቢያ በጋዜጠኛነት መቀጠራቸው ተሰምቷል
ቦሪስ ጆንሰን በቴሌቪዥን ጣቢያው የዜና አቅራቢ እና ተንታኝ በመሆን ነው የሚቀላቀሉት
የብሪታኒያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጋዜጠኝነት ተቀጥረው ሊሰሩ መሆኑ ተንሯል።
ቦሪስ ጆንሰን ጂቢ ኒውስ “GB News” የቴሌቭዥን ጣቢያ በጋዜጠኛነት ለመስራት ጣቢያውን መቀላቀላቸው አስታውቀዋል።
ጆንሰን በቴሌቪዥን ጣቢያው የዜና አቅራቢ፣ አዘጋጅ እና ተንታኝ ይሆናሉ ተብሏል።
ቦሪስ ጆንሰን በበቀድሞ ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ገጻቸው በለቀቁት የቪዲዮ መልእክት “ጂቢ ኒውስን እንደምቀላቀል ስነግራችሁ በደስታ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
"በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የእኔን ትክክለኛ አስተያየት እና እይታ እብደማቀርብላችሁ ቃል እገባለሁ” ብለዋልቦሪስ ጆንሰን በለቀቁት ቪዲዮ ላይ ብለዋል
በቀጣ የአሜሪካና የብሪታኒያ ምርጫ በመዘገብ “ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ” የተባለላቸው ቦሪስ ጆንሰን፤ “እንግሊዝ በዓለም ስላላት ዕምቅ አቅምና ፈተናዎቻችንም እናገራለሁ” ሲሉ አክለዋል።
የቀድሞው ጋዜጠኛ እና የለንደን ከንቲባ የነበሩት ቦሪስ ጆንሰን ቴሬዛ ሜይን በመተካት ብሪታንያን ከፈረንጆቹ 2019 እስከ አሳለፍነው ነሀሴ ወር ጠቅላይ ሚንስትር ነበሩ።
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን ህግ ተላልፈዋል፣ ይዋሻሉ እና ሌሎች ያልተገቡ ባህሪያት አሏቸው በሚል የሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት ጫና አሳድረውባቸው ነው ስልጣን ለመልቀቅ የተገደዱት።