ቦሪስ ጆንሰን የጣሉትን ጥብቅ የእንቅስቃሴ እገዳ የተላለፉ አማካሪያቸውን እንዲያነሱ የቀረበውን ጥያቄሳይቀበሉ ቀሩ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካሪው የጥንቃቄ መርሆዎችን አክብረው ተንቀሳቅሰዋል ያለ ሲሆን ከቤተሰባቸው አለመቀላቀላቸውን አስታውቋል
አማካሪው እገዳውን በመተላለፍ 4 መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ቤተሰባቸው ጠይቀዋል ተብሏል
የጣሉትን ጥብቅ የእንቅስቃሴ እገዳ የተላለፉ አማካሪያቸውን እንዲያነሱ የቀረበውን ጥያቄ ቦሪስ ጆንሰን ሳይቀበሉ ቀሩ
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጣሉትን ጥብቅ የእንቅስቃሴ እና የጉዞ እገዳ በመተላለፍ ወደ ቤተሰባቸው አቅንተዋል የተባሉ አማካሪያቸውን ከኃላፊነት እንዲያነሱ የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል፡፡
የ2016ቱን የእንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት የመነጠል ሂደት (ብሬግዚት) በበላይነት የመሩት ዶሚኒኪ ከሚንግስ 400 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በሰሜናዊ እንግሊዝ ዱርሃም ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ያቀኑት ጆንሰን እገዳውን ባስተላለፉበት ባሳለፍነው ወርሃ መጋቢት ነበር፡፡
በወቅቱ የከሚንግስ ባለቤት የኮሮና ህመም ምልክቶችን ያሳዩ ነበር የተባለ ሲሆን የአንድ ልጃቸውን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ቤተሰባቸው ማቅናታቸውም ይነገራል፡፡
ሆኖም የልጃቸውን ሁኔታ ቤተሰባቸው ሊከታተል እንደሚችል የሚናገሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እገዳውን በመተላለፋቸው ከኃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ግን ጥያቄውን አልተቀበለም ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ፡፡
አማካሪው የጥንቃቄ መርሆዎችን አክብረው የልጃቸውን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ቤተሰባቸው ቢያቀኑም በአጎራባች መንደሮች ሆነው ሁኔታዎችን ከመከታተል ውጪ ከቤተሰባቸው እንዳልተቀላቀሉም አስታውቋል፡፡
ከአማካሪያቸው ጉዞ ጥቂት ቀናት በፊት እገዳ ስለመጣላቸው አስታውቀው የነበሩት ጆንሰን ራሳቸው በቫይረሱ ተይዘው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡