የቀድሞ የብሪታኒያ መሪ ቦሪስ ጆንሰን “ፑቲን የሚሳይል ጥቃት እንደሚሰዘር ዝቶብኝ ነበር” አሉ
ቦሪስ ጆንሰን፤ ፑቲን "አንተን በሚሳይል ለመምታት አንድ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስደው" ሲል እስፈራርቶኛልም ብለዋል
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ጆንሰን የተናገሩት ነገር “ውሸት” ነው ሲሉ ተናግረዋል
የቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጂንሰን ሰልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ከወሰደች ነገሮች ወደ ከፋ ሁኔታ እንደሚያቀኑና ለፑቲን ሲያሳስቧቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ዩክሬንም ብትሆን "በቅርብ ጊዜያት የኔቶ አባል እንደማትሆን "ለፑቲን ቃል በመግባት ደም አፋሳሽ ጦርነቱን ለማስቀረት በርካታ ጥረቶች ሲያደርጉ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ በክሬምሊን ባለስልጣናት በኩል የዩክሬን አጋር ተደርገው የሚወሰዱት የቦሪስ ተማጽኖ ለፑቲን የሚዋጥ አልነበረም ፡፡
በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየካቲት 2022 ኪቭ የጎበኙበት አጋጣሚ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ያበሳጨ እንደነበር የቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተናግረዋል፡፡
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሚሳይል ጥቃት እንደሚሰዘር ዝቶብኝ ነበርም ያሉት ቦሪስ ጆንሰን፡፡
የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር የነበራቸውን ንግግር በተመለከተ ከቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ጋር ቆይታ ያደረጉት ቦሪስ ጆንሰን፤ ፑቲን የዛቱባቸው በአንድ ወቅት በነበራቸው “ያልተለመደና ዘለግ ያለ የስልክ ለውውጥ” እንደነበር ገልጸዋል፡፡
"ቦሪስ አንተን መጉዳት አልፈልግም፤ ነገር ግን በሚሳይል ለመምታት አንድ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስደው" ሲል እስፈራርቶኛልም ብለዋል ፡፡
በጉዳይ ላይ ያላቸውን አስተያየት የተጠየቁት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ጆንሰን የተናገሩት ነገር “እውነት አይደለም” ወይም “ ሆነ ተብሎ የተጠነሰሰ ውሸት” ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"ሚሳኤሎችን የመጠቀምና የማስፈራራት ነገር አልነበርም" ሲሉም አክለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
የሩሲያ እና ብሪታኒያ ዲፕማሲያዊ ግንኙነት እምብዛም የሚነገርለት አለማሆኑ ይገለጻል፡፡
በተለይም የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ ሰርጌ ስክሪፓል እንደፈረንጆቹ 2018 በብሪታንያ ሳሊስበሪ ከተማ ተመረዘ በኋላ በሞስኮ እና በለንደን መካከል ያለው ግንኙነት ፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት ባሉት አስርት ዓመታት ውስጥ እጅግ ሻክሮ መቆየቱ ይታወቃል፡፡