ህጉ ለግል ጥቅም ሶስት የካናቢስ እፆችን ማብቀልን እና እስከ 25 ግራም የሚመዝን ካናቢስ መያዝ ይፈቅዳል
ጀርመን ካናቢስን ህጋዊ ካደረጉ ሀገራት ጎራ ተቀላቀለች።
ጀርመን፣ በንደስታግ የተባለው ህግ አውጭ አካል ግለሰቦች እና ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች እንዲያበቅሉ እና የተወሰነ መጠን ያለው ካናቢስ እንዲይዙ የሚፈቅድ ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ካናቢስን ህጋዊ ካደረጉ ጥቂት ሀገራት ጎራ ተቀላቅላለች።
የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በሆነው የሶስት ፓርቲዎች ጥምረት ገዥ ፓርቲ የጸደቀው ህግ ለግል ጥቅም ሶስት የካናቢስ እፆችን ማብቀልን እና እስከ 25 ግራም የሚመዝን ካናቢስ መያዝ እንደሚፈቅድ ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ህግ ጎልማሳዎች ለሆኑ እና ከ500 በላይ ያልበለጡ አባላት ላሏቸው የመዝናኛ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ካናቢስ እንደመይዙ ይፈቅዳል።
በህጉ መሰረት ከመዝናኛ ቤቱ አባል ውጭ የሆነ ሰው ለመዝናኛ ቤቶች ከተመደበው ካናቢስ መጠቀም አይችልም።
የጀርመን የጤና ሚኒስትር ካርል ላውተርባች "ሁለት ግቦች አሉን። የጥቁር ገበያ ግብይትን ለማጥፋት እና የህጻናት እና የወጣቶችን ጥበቃ ለማጠናከር ነው" ብለዋል።
ነገርግን ተቃዋሚዎችን ህጉ የዕፅ መጠቀምን ያበረታታል ሲሉ የሚኒስትሩን ሀሳብ ተቃውመዋል።
ሚኒስትሩ ይህ "ራሳችንን አሸዋ ውስጥ እንደመቅበር ይቆጠራል"፤ ካናቢሰን እየተጠቀሙ ያሉ ወጣች ቁጥር መጨመሩን ማወቅ አለብን ሲሉ ትችቱን አይቀበሉትም።
በጀርመን 4.5 ሚሊዮን ሰው ካናቢስን ይጠቀማሉ።
በአሜሪካ እና በአውስትራሊያ በተወሰኑ ግዛቶች ህጋዊ የሆነውን ካናቢስ ህጋዊ በማድረግ ጀመርን ዘጠነኛ ሀገር ሆናለች።
በርካታ ሀገራት በማስታገሻነት ለመድሃኒትነት ይጠቀሙታል።
ካናቢስ ታዳጊ ወጣቶች እንዲጠቀሙት አይፈቀድም፣ በትምህርት ቤቶች እና በመጨዋቻ ቦታዎች አሁንም ክልክል ነው።