የብራድ ፒት እና አንጀሊና ጁሊ ሴት ልጅ ለምን በአባቷ ስም መጠራት አቆመች?
የተዋናዮቹ ሁሉም ልጆች የብራድ ፒትን ስም ከአባትነት ሰርዘዋል
ዝነኛ ተዋናዮቹ ብራድ ፒት እና አንጀሊና ጁሊ ከኢትዮጵያ በማደጎ የተወሰደችው ዛህራን ጨምሮ ስድስት ልጆች አሏቸው
የብራድ ፒት እና አንጀሊና ጁሊ ሴት ልጅ ለምን በአባቷ ስም መጠራት አቆመች?
በርካታ ፊልሞች ለይ በመተወን የሚታወቁት ዝነኞቹ ብራድ ፒት እና አንጀሊና ጁሊ ከኢትዮጵያ በማደጎ የወሰዷትን ዛህራን ጨምሮ ስድስት ልጆች ነበራቸው፡፡
ጥንዶቹ በጋብቻ በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ የወለዷት እና ብቸኛ ት ልጃቸው የ18 ዓመቷ ሺሎህ በአባቷ ስም እንዳትጠራ በፍርድ ቤት ማስወሰኗን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ከሺሎህ በተጨማሪም ቀሪዎቹ ሁሉም ልጆች በአባታቸው ቦታ የእናታቸው አንጀሊና ጁሊ ስም እንዲካተት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ዝነኞቹ በፈረንጆቹ 2014 በይፋ ህጋዊ ጋብቻ መስርተው ነበር የተባለ ሲሆን በአንጀሊና ጁሊ ጥያቄ መሰረት በ2019 ትዳራቸው በፍቺ ተጠናቋልም ተብሏል፡፡
የጥንዶቹ እውነተኛ ልጅ እና የማደጎ ልጆች ሁሉም ከአንጀሊና ጁሊ ጋር እንደሚኖሩ የጠቀሰው ዘገባው አባታቸው እናታቸው እና በእነሱ ላይ ያልተገቡ ጫናዎችን እና በደሎችን ማድረሱ ብራድ ፒትን እንደ አባት ላለመጠራት ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡
መልክሽ ለቴሌቪዥን አይመጥንም የተባለችው እንስት ዝነኛ የኪነ ጥበብ ሽልማቶችን አሸነፈች
ተዋናዮቹ በትዳር በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ በፈረንሳይ የወይን አምራች ድርጅት የመሰረቱ ሲሆን አንጀሊና ጁሊ ይህን የወይን ኩባንያ ድርሻ መሸጥ ብትፈልግም የቀድሞ ባለቤቷ ብራድ ፒት ጫና እያደረገባትም ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አንጀሊና ጁሊ ስለ ብራድ ፒት በትዳር ውስጥ በነበሩባቸው ጊዜ ውስጥ ያሳይ ስለነበረው ባህሪ እና ድርጊት ለሚዲያ እንዳትናገር ውል እንድትፈርም አድርጓል መባሉ ልጆቹ ፊት እንዲነሱት ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ልጆቹ በስሙ እንዳይጠራ በመፈለጋቸው እንዳዘነ የተገለጸው ብራድ ፒትም በጉዳዩ ማዘኑን በተለይም ሺሎህ የተሰኘችው ሴት ልጁ ስሙ ከአባትነት እንዲፈሰረዝ ማድረጓ እንዳበሳጨው ተጠቅሷል፡፡