ብራዚል በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች
በባለፈው ሳምንት የብራዚሊያው ድራማ እጃቸው አለበት የተባሉ የፓሊስ አዛዦች እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው በቁጥጥር ስር የሚውሉት
ከአመፁ በኋላ 1 ሺህ 500 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዠያዋለችው ብራዚል፥ በቀጣዮቹ ቀናት ክስ መመስረት ትጀምራለች
ብራዚል በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች
የብራዚል የፍትህ ተቋማት በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣታቸው ተነግሯል።
ባለፈው ሳምንት በመዲናዋ ብራዚሊያ ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተገናኘ ተሳትፎ አድርገዋልጰተብለው የተጠረጠሩ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸው።
በብራዚሊያው ድራማ ነገሮችን በቸልታ አልፈዋል በሚል በፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ የየተዠዠተተቹ የፓሊስ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ከሚውሉት መካከል ናቸው።
በዛሬው እለት ስማቸው ያልተጠቀሰ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከብራዚሊያ የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ ደጋፊዎች በብራዚሊያ ለቀሰቀሱት አመፅ ተጠያቂነት አለባቸው ከተባሉት ውስጥ የከተማዋ የደህንነት ሹም የነበሩት አንደርሰን ቶሬዝ አንዱ ናቸው።
ቶሬዝ "የተቀነባበረ ሴራ በመፈፀም" በብራዚል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተጠያቂ ቢደረጉም ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ብለዋል።
የፓሊስ አዛዡ ኮሎኔል ፋቢዬ አውጉስቶም አመፁን መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
አውጉስቶ በዛሬው እለት የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸው ግን አልታወቀም።
ብራዚል ከድራማዊው አመፅ በኋላ 1 ሺህ 500 ሰዎችን በፖሊስ አካዳሚ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውላለች።
ሌሎች 600 የአመፁ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ሰዎችም በተለያዩ ስፍራዎች በእስር ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በቀናት ውስጥ ክስ መመስረት እንደምትጀምር ተገልጿል።